Connect with us

አቃቤ ሕግ በአብይ አበራ አለምነህ ላይ አቋርጦት የነበረውን ክስ አንቀሳቀሰ

አቃቤ ሕግ በአብይ አበራ አለምነህ ላይ አቋርጦት የነበረውን ክስ አንቀሳቀሰ
Photo: Ethiopian Reporter

ህግና ስርዓት

አቃቤ ሕግ በአብይ አበራ አለምነህ ላይ አቋርጦት የነበረውን ክስ አንቀሳቀሰ

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በአቶ አብይ አበራ አለምነህ እና በድርጅቱ አዲስ ቪው ጄኔራል ቢዝነስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ላይ አቋርጦት የነበረውን ክስ ማንቀሳቀሱ ተገልጿል፡፡

እንደ ተቋሙ መረጃ ተከሳሹ ከዚህ በፊት በተለያዩ ወንጀሎች አቃቤ ሕግ የመሰረተበትን ክስ በመቃወም በተደጋጋሚ ያቀረበውን አቤቱታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ጠቅላይ አቃቤ ህግ ላልተወሰነ ጊዜ ክሱን አቋርጦት የነበረው።

አቃቤ ሕግ ከፖሊስ ጋር በመሆን ክሶቹ ላይ ተገቢውን ማጣራት ካደረገ በኋላ በተለያዩ ወንጀሎች በግለሰቡና በድርጅቱ ላይ አቋርጦት የነበረውን ክስ ማንቀሳቀስ ጀምሯል።

እንዲንቀሳቀሱ ከተደረጉ ክሶች መካከል አራጣ፣ ግብር ማጭበርበር፣ በህገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ የፀና ንግድ ፍቃድ ሳይኖር የጦር መሳሪያ ኮሚሽን ኤጀንትነት እና ሃሰተኛ ሰነድ የሚሉት ወንጀሎች ይጠቀሳሉ።

እንደ አቃቤ ሕግ መረጃ በግለሰቡና በድርጅቱ ላይ በሌሎች ከባድ ወንጀሎች ላይም ምርመራ እየተካሄደ ይገኛል።

በአዲስ ቪው ጄኔራል ቢዝነስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ባለቤቱ አብይ አበራ አለምነህ ጉዳይ እየተመለከተ ያለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ተኛ የወንጀል ችሎት ነው።

(ምንጭ :-ኢቲቪ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top