Connect with us

የኢትዮጵያን ቡና በርካሽ ዋጋ የሚሸጡ አካላት ሊታገዱ ነው

የኢትዮጵያን ቡና በርካሽ ዋጋ የሚሸጡ አካላት ሊታገዱ ነው
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የኢትዮጵያን ቡና በርካሽ ዋጋ የሚሸጡ አካላት ሊታገዱ ነው

የራሳቸውን ጥቅም በማስቀደም ቡናን ከገዙበት ዋጋ በታች በመሸጥ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ገበያ ዋጋው እንዲያሽቆለቁል እያደረጉ ያሉ አካላት ሊታገዱ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የዘርፉ ኃላፊ አቶ ሻፊ ዑመር በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያ ቡና ላለፉት አምስት ዓመታት በዓለም አቀፍ ገበያ ያለው ዋጋ እንዲያሽቆለቁል ካደረጉት አበይት ምክንያቶች መካከል፤ ጥቅማቸውን ወደ አገር ውስጥ በሚያስገቡት ምርት ለማካካስ ብለው ቡናን በርካሽ ዋጋ ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚያቀርቡ አካላት ዋነኞቹ ናቸው።

ችግሩን ለመፍታት በዚህ ህገ ወጥ ሥራ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ቡና ላኪዎች እስከ መታገድ የሚያደርስ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

እንደ አቶ ሻፊ ገለጻ፤ የአገር ውስጥ የቡና ዋጋ ከፍ ቢልም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ዋጋ ግን እየቀነሰ ይገኛል። የኢትዮጵያ ቡና ዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ ማሽቆልቆሉ የግብይት ሥርዓቱ ላይ ችግር ፈጥሯል።

ቡናን ከገዙበት ዋጋ በታች የሚሸጡ ህገ ወጥ ላኪዎች መበራከታቸው፤ የቡና ኮንሮባንድ መኖሩ፤ በቡና አቅርቦት ላይ ቡናን ወደ ውጭ በመላክ ‹‹ዶላር እናገኛለን የሚል እምነት›› አለመኖርና የአገር ውስጥ ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም የኢትዮጵያን ቡና ዋጋ በዓለም አቀፍ ገበያ እንዲቀንስ አድርጎታል። ይህንን ተከትሎም በዓለም አቀፍ ገበያ ዋጋውን ከፍ ማድረግ አልተቻለም።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top