Connect with us

ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ተከሰሱ

ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ተከሰሱ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ተከሰሱ

በባህርዳርና አዲስ አበባ ከአማራ ክልል አመራሮችና ከእነ ጀነራል ሰዓረ መኮንን ግድያ ጋር በተያያዘ በወንጀል ድርጊቱ “እጃቸው አለበት” በሚል የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው።

የጀነራል ሰዓረ ጥበቃ የነበረው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡን ጨምሮ 13ቱም ተከሳሾች ዛሬ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ ተነቦላቸዋል።

ተጠርጣሪ ተከሳሽ አስር አለቃ መሳፍንት ችሎቱ የሚጠይቀውን ምላሽ መስጠት እንዳልቻለና “እሺ” እና “አዎ” የሚሉ ምላሾችን ብቻ እንደሚሰጥ ሪፖርተራችን ከችሎቱ ቦታ ዘግቧል።ችሎቱ “መናገር ካልቻልክ ሀሳብህን በፅሁፍ ግለፅ” ቢለውም ተከሳሹ ይህንንም አለመቻሉ ተመልክቷል።

ከሰኔ 15ቱ ወንጀል ጋር በተያያዘ ባህርዳር ላይ የአማራ ክልል አመራሮች አቶ አምባቸው መኮንን፣ አቶ ምግባሩ ከበደና አቶ እዘዝ ዋሴ ሲገደሉ እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ ደግሞ የኢፌዴሪ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጀነራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ መገደላቸው ይታወሳል።

ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ከተመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች መካከል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ይገኙበታል።

ዓቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ ” ህገ መንግስትን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ነው ክሱን የመሰረተባቸው።

ተከሳሾቹ “በማረፊያ ቤት የደህንነት ስጋት አለብን” በሚልም ለችሎቱ አቅርበዋል፣በመምርመር ወቅት የተወሰዱባቸው ንብረቶች እንዲመለሱላቸውም ጠይቀዋል።

ተከሳሾቹ ለቀረበባቸው ክስ የመቃወሚያ ምላሻቸውን ለታህሳስ 1፣2012 እንዲያቀርቡ ችሎቱ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን፣ ከደህንነት ጋር ላነሱት ጉዳይ በማረሚያ ቤት ሆነው ጥብቅ ጥበቃ እንዲደረግላቸውም ችሎቱ አዟል።ለምርመራ በሚል ስለተወሰዱባቸው ንብረትም በዝርዝር ለችሎቱ እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ አዟል።

(ምንጭ ኢቲቪ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top