Connect with us

እመጓን ፍለጋ፤ ሞላሌ የመንዝ ማማዎች ጌጥ

እመጓን ፍለጋ፤ ሞላሌ የመንዝ ማማዎች ጌጥ

ባህልና ታሪክ

እመጓን ፍለጋ፤ ሞላሌ የመንዝ ማማዎች ጌጥ

እመጓን ፍለጋ፤ ሞላሌ የመንዝ ማማዎች ጌጥ፤

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ታሪካዊቷን የእመጓ ቤተ ክርስቲያን ፍለጋ ወደ መንዝ ወርጃለሁ ይለናል፡፡ በመንዝ ማማ ዋና ከተማ በሞላሌ ያደረገውን ቆይታ የትረካው መጀመሪያ አድርጎታል፡፡ | ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ይበርዳል ግን ደግሞ እንደ መሀል ሜዳ አይደለም፡፡ ከአምስቱ መንዞች አንዷ በኾነችው ማማ ምድር ነኝ፡፡ የመንዝ ስም ምድርን ያስከትላል፡፡ ማማ ምድር፣ ጌራ ምድር፣ ቀያ ምድር፣ ላሎ ምድር፤ መንዝ ግሼ ከአምስቱ መንዞች በቁጥር አንዷ ናት፡፡ ሞላሌ ሰው አታጣም፡፡ ዘብር ገብርኤልን ብሎ የመጣ ሲመጣም ሲሄድም ያርፍባታል፡፡

መንገዷ ዛሬም አበሳ ነው፡፡ ከተማዋ ግን እየሞቀች ነው፡፡ እዚህም እዚያም ፎቅ ይታያል፡፡ እነኚህን ፎቆች ያበዙላት ዘንድ ተመኘሁ፡፡ ሰው ፎጣ ለብሷል፡፡ ከንፈር የሚሰነጥቀው ብርድ ጥቅምት ይብሳል፡፡ ዙሪያው በቀደሙ ገዳማት የታጠረ ነው፡፡ መንዝ መንዛት ከሚለው የመጣ ነው፡፡ ቃሉ ከክርስቶስ ደም መረጨት ጋር ይገናኛል፡፡ የታላላቆቹ ገዳማት መገኛ ነው፡፡

እዚህ ሁለትና ሦስት መቶ ዓመት እድሜ ማስቆጠር ከቀደሙት አያስቆጥርም እዚህ ብዙ መቶዎችን መኖር ብርቅ አይደለም፡፡ እመጓን ፍለጋ ነው የመጣሁት፡፡ እመጓን ፍለጋ የመጣ ሞላሌ አድሮ መሄድ ግድ ይለዋል፡፡ ሞላሌ ያደረ ደግሞ የማማዎችን ጌጥ የስስታቸውን ከተማ እንደልቡ ያያታል፡፡

ፍስክ የደረሰ ሁሉ ነገር ቀላል ነው፡፡ ያን ጦስኝ የበላ በግ በግላጭ ለማግኘት ይረዳል፡፡ መንዞች እምነት አጥባቂ ናቸው፡፡ በፆም ያን በግ ልቅመስ ብሎ መመኘት ሞኝነት ነው፡፡ እዚህ እምነት በአፍ ብቻ ሳይኾን በተግባርም ከፍ ብሏል፡፡ ቤቶቻቸው ደስ ይላሉ፡፡

የመንዝ ባህላዊ መንደሮችን ያየ ሞላሌ ሲደርስ ለምን ያ የጎጆ አሻራ ዘምኖ አላየውም ሲል ይቆጫል፡፡ ሞላሌ አዲስ አበባንና ደብረ ብርሃንን ለመመስል የምትመኝ ከተማ ስለሆነች የባህላዊ ቤታቸው አሻራ አይታይባትም፡፡

እኔ ግን እመክራታለሁ ራስን እየመሰሉ መዘመን፣ የራስ ጥበብን ማግዘፍ፣ የራስ ዲዛይንን ከፍ ማድረግ ስልጣኔ እንደሆነ፡፡ ሊቀ ካህናት ኢሳያስ የወረዳው ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊ ናቸው፡፡ ቀጠሯቸውን አክብረው መጡ፡፡ የቆምኩት ሀረር ሆቴል የሚል ጽሑፍ ያለበት የሞላሌ ከተማ ጎዳና ላይ ነው፡፡ ጉዞ ወደ እመጓ ይቀጥላል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top