Connect with us

የጤና ሚኒስትሩ አሚን አማን መልዕክት

የጤና ሚኒስትሩ አሚን አማን መልዕክት
Photo: Facebook

ጤና

የጤና ሚኒስትሩ አሚን አማን መልዕክት

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጥር ወር 2011 ዓ.ም ባጸደቀው አዋጅ ቁጥር 1112/2011 መሰረት ሲጃራና አጠቃላይ የትምባሆ ምርቶች አጠቃቀም የሚያደርሰውን የጤና ጠንቅ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የህግ ግዴታዎችንና ክልከላዎችን ጥለዋል፡፡

ሲጋራ እና ሌሎች የትምባሆ ምርቶችን ማጨስን አስመልክቶ የተጣላ ክልከላ
ለማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ክፍት የሆኑ እንደ ሆቴል፣ ሬስቶራንት፣ ምግብ ቤት፣ መጠጥ ቤት እና የምሽት ቤት በመሳሰሉ ማንኛውም ድርጅቶች ፡-
• ከበር መልስ ባሉ ቦታዎች እንዲጨስ መፍቀድ፤ እንዲህም
• በነዚህ ቦታዎች በአስር (10) ሜትር ዙሪያ እንዲጨስ መፍቀድ፤
• በነዚህ ቦታዎች ውስጥ የሲጃራ መተርኮሻ ወይም ሌላ የትምባሆ ምርትን ለመጠቀም የሚያገለግል ማንኛውም እቃ ማስቀመጥ የተከለከለ ነው፡፡

በተጨማሪ ድርጅቶቹ በጉልህ የሚታይ ትምባሆ ማጨስ ወይም መጠቀም የተከለከለ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ ከነባለቀለም ምልክቱ በድርጅቱ ውስጥ የመለጠፍ ግዴታም አለበት፡፡

ከበር መልስ ያሉ የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ላይ ወደ 29.3 በመቶ የሚሆኑ ቀጥተኛ አጫሽ ያልሆኑ ሰዎች ለትንባሆ ጭስ ተጋላጭ ናቸው::
የትንባሆ ጭስ አንድ ጊዜ ከተጨሰ በኃላ ለአምስት ሰአታት አየር ላይ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ንጥረነገሮች ይቆያሉ::

በመሆኑምማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል የራሱ እና የአካባቢውን ጤና ለመጠበቅ ቅድሚያ ሀላፊነት እንዲወስድ አደራ ማለት እንወዳለን::

ከላይ የተቀመጠውን የእገዳ ህግ የተላለፈ የህዝብ መገልገያ ሲያዩ በ 8482 ነፃ የስልክ መስመር ወደ የኢትዮጵያ የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን ወይንም በ8864 የአዲስ አበባ የምግብ፣ መድኃኒት እና ጤና ክብካቤ ባለስልጣን እንዲሁም በወረዳ በክፍለ ከተማ እና በክልል የቁጥጥር ባለስልጣን በማመልከት ድርጅቶቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ ትተባበሩን ዘንድ አደራ ማለት እወዳለሁ::

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top