Connect with us

በቂ እንቅልፍ የማይተኙ ሰዎች በሌሎች ዘንድ ተፈላጊታቸዉ ይቀንሳል – አዲስ ጥናት

በቂ እንቅልፍ የማይተኙ ሰዎች በሌሎች ዘንድ ተፈላጊታቸዉ ይቀንሳል፡ አዲስ ጥናት
Photo: Facebook

ጤና

በቂ እንቅልፍ የማይተኙ ሰዎች በሌሎች ዘንድ ተፈላጊታቸዉ ይቀንሳል – አዲስ ጥናት

በየዕለቱ በቂ እንቅልፍ የማይተኙ ሰዎች በሌሎች ዘንድ ተፈላጊና ተወዳጅ የመሆን እድላቸዉ የቀነሰ ነዉ ሲል አንድ ጥናት ይፋ አደረገ ሲል ኢንተርፕረነር ዶት ቾም የተባለዉ ድረ ገፅ አስነብቧል፡፡

ሮያል ሶሳይቲ ኦፕን ሳይንስ በተሰኘዉ ጆርናል ላይ የታተመዉ ይህ ጥናት እንደሚያመለክተዉ ከሆነ በቂ እንቅልፍ ያላገኙ ሰዎች አስደሳችና ጤናማ ገጽታ ስለማይኖራቸዉ በሌሎች ዘንድ ተፈላጊ የመሆን እድላቸዉ አነስተኛ ነዉ፡፡ ይህም በሌሎች ዘንድ የመወደድ እድላቸዉን ይቀንሰዋል ሲል ጥናቱ ያመለክታል፡፡

አንቅልፍ ከማጣት ጋር ተያይዞ የሚፈጠረዉ የድካም ስሜትከመጫጫንና ከጤንነት መዛባት ያለፈ ጉዳት ያስከትላል፡፡ ብዙዎች ይላል ጥናቱ ብዙዎች እንዲህ ያለ ስሜት የሚታይባቸዉን ሰዎች የመቅረብ ፍላጎታቸዉ እጅግ አነስተኛ ነዉ፡፡

በስዊዲን ሀገር ካሮሊንካ ኢንስቲትዩት በተካሄደዉ በዚህ ጥናት ተማራማሪዎች 25 ሴትና ወንድ ተማሪዎችን ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለስምንት ሰዓታት አንቅልፍ እንዲያገኙ ካደረጉ በኋላ ከመኝታቸዉ እንደተነሱ ምንም አይነት ሜካፕ ሳይጠቀሙ ፎግራፍ አነሷቸዉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህኑ ተማሪዎች ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለአራት ሰዓታት ብቻ እንዲተኙ በማድረግ ሌሎች ፎቶግራፎች እንዲነሱ ተደረገ፡፡

በመቀጠል አጥኝዎች የተማሪዎቹን ፎቶግራፍ በመሰብሰብ ተማሪዎቹን ከዚህ በፊት ለማያዉቋቸዉ 122 ሰዎች በመስጠት ሳቢነት (ማራኪ) ፤ ጤናማ ገፅታ፤ የእንቅልፍ ስሜትና ታማኝነትን መሰረት በማድረግ ነጥብ እንዲሰሰጡ አደረጓቸዉ፡፡

በሚገርም ሁኔታ አብዘሃኛዎቹ ሰዎች ተማሪዎቹ በቂ እንቅልፍ ሳያገኙ ለተነሷቸዉ ፎቶግራፎች የሳቢነትና የጤናማነት ገፅታ ነጥብ እጅግ ዝቅተኛ ነበር፡፡

እንደ ጥናቱ ከሆነ ነጥብ ሰጭዎቹ የእንቅልፍ እጦት የማይታይባቸውን ሰዎች ለመቅረብና ለመተዋወቅ የነበራቸው ፍላጎት ዝቅተኛ ነበር። ከዚህም ባለፈ ሰዎች እንዲህ ያሉ ሰዎችን መቅረብ የማይፈልጉት ከጤና ጋራ የተያያዙ ጉዳዮችን ለማስወገድ እንደሆነም ጥናቱ አረጋግጦል።

በእንቅልፍ ማጣትም ሆነ በሌላ ምክኒያት ጤናማ ያልሆነ እና የተዳከመ የፊት
ገፅታ የሠዎች የማህበራዊ ት ስ ስር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረውም
ተገልፆል።

ሆኖመ ግን በቂ እንቅልፍ ማጣት በሌሎች የመፈለግ ሀኔታ ላይ ተጽዕኖ ቢኖረዉም በሰዎች ዘንድ የሚኖር አመኔታ ላይ ግን ምንም ለዉጥ እንዳልነበረዉ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top