Connect with us

የአርበኞች ማህበር ባለ አስር ፎቅ ህንፃ ያስገነባል

የአርበኞች ማህበር ባለ አስር ፎቅ ህንፃ ያስገነባል
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

የአርበኞች ማህበር ባለ አስር ፎቅ ህንፃ ያስገነባል

የጥናታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትብብር ባገኘው 564 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ባለ አስር ፎቅ ህንፃ ለማስገንባት ማቀዱን አስታወቀ።

የማህበሩ ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፤ ማህበሩ አራት ኪሎ በሚገኘው ጽህፈት ቤቱ አጠገብ በተሰጠው ቦታ ላይ ግንባታውን ለማካሄድ የሚያስችለውን ፈቃድ አግኝቷል፤ ለግንባታውም ጨረታ ለማወጣት እየተዘጋጀም ነው።

እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለፃ፤ ለህንፃው ግንባታ ፕሮጀክት ከ80 እስከ 100 ሚሊየን ብር እንደሚ ያስፈልግ በጥናት ተለይቷል። የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ከኅብረተሰቡ በተለያየ መንገድ በተሰበ ሰበው ወደ 25 ሚሊዮን ብር ግንባታው የሚጀመር ይሆናል።

በጦርነቱ ጊዜ አርበኞች ብቻ ሳይሆኑ ኅብረተሰቡ ተባብሮ የሀገሪቷን ነፃነቷ ማስከበሩን አመልክተው፣ በውስጥ አርበኞች ድጋፍ ህዝቡ መረጃ እያቀበለ የጠላት ጦር እንዲፈታ ማደረጉን አስታውሰዋል። አሁንም እጃችንን ወደ ኅብረተሰቡ መዘርጋታችን አይቀርም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የከተማዋ አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሌ ኮም፣ መብራት ኃይል እና ሌሎች የግልና የመንግሥት ባንኮች እንዲሁም መሥሪያ ቤቶችና ባለሀብቶች ለግንባታው ድጋፍ በማድረግ አሻራቸውን እንዲያኖሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ህንፃው መጪው ትውልድ ኢትዮጵያ አኩሪ ታሪክ እንዳላት እና እንዴት እንደ ተመሠረተች የሚታይበት ቤተመዘክርና ቤተመፃህፍት፣ ከዋክብት የሚታዩበት ፕላኒቴሪየም ኦዲቴሪየምና አዳራሾች ገቢ ሊያስገኙ የሚችሉ መኖሪያ ቤቶች እንደሚኖሩትም ፕሬዚዳንቱ አብራርተዋል። ‹‹በዚህም ወጣቶችንም እየሰበሰብን ታሪክ እናስተም ርበታለን›› ብለዋል። ሚካኤል ሽፈራው የሚባል ባለሙያ የህንፃ ውን ዲዛይን በትብብር መሥራቱንም ካገኘነው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

አዲስ ዘመን ህዳር 9/2012

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top