Connect with us

የአረብ ሊግ ፓርላማ ግብጽን ወግኖ ለጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ደብዳቤ ጻፈ

የአረብ ሊግ ፓርላማ ግብጽን ወግኖ ለጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ደብዳቤ ጻፈ
Photo: Facebook

ዜና

የአረብ ሊግ ፓርላማ ግብጽን ወግኖ ለጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ደብዳቤ ጻፈ

~አሜሪካ፤ በግብጽ የተዋጊ ጀቶች ሽመታ ተቆጣች፣

የአረብ ሊግ ፓርላማ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ፓርላማ አፈጉባኤ ደብዳቤ መጻፉን የግብጹ አህራም ኦንላይን ዘግቦታል፡፡ ፓርላማው በደብዳቤው ከሱዳንና ግብጽ ጎን እንደሚቆም አመልክቷል፡፡

የግብጽና የሱዳን የውሀ ጥቅም መነካት እንደሌለበት የጠቀሰው ፓርላማው በህዳሴ ግድብ ሙሌት ዙሪያ ፍትሀዊ ስምምነት ሶስቱ ሀገራት እንዲያደርጉ ማሳሰቡን ዜናው ይገልጻል፡፡

የሊጉ ፓርላማ አፈጉባኤ ፋህም አል-ሰላሚ በትዊተር ገጻቸው ላይ ይህንኑ የደብዳቤ ልውውጥ ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚሁ ትዊታቸው ላይ ኢትዮጵያ የግብጽንም ሆነ የሱዳንን ጥቅሞች እንድትጠብቅ በዳብዳቤያቸው ላይ ማስፈራቸውን አመልክተዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ግብጽ
ከራሽያ 20 የተዋጊ ጀቶችን ልትገዛ ነው መባሉን ተከትሎ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ መስጠቷ ተሰምቷል።

ግብጽ በሁለት ቢሊዮን ዶላር ወጪ 20 ተዋጊ ጀቶችን (Sukhoi Su-35 ) ከሩስያ ልትገዛ በዝግጅት ላይ መሆንዋ መሰማቱ የአሜሪካ መንግሥትን አስቆጥቷል። ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው የግብጽ እርምጃ በሁለቱ አገሮች መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን ወታደራዊ ግንኙነትና ትስስር የሚጎዳ ነው።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top