Connect with us

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምፅ አሰጣጥ ነገ ይከናወናል

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምፅ አሰጣጥ ነገ ይከናወናል
Photo: Facebook

ዜና

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምፅ አሰጣጥ ነገ ይከናወናል

~ማንኛውም የድጋፍ እና የተቃውሞ ሰልፍ ተከልክሏል፣
~ በሀዋሳ የሞተር ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ለሶስት ቀናት ተከልክሏል፣

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በሰላም እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ዞን የፀጥታ መምሪያዎች አስታውቀዋል።

መምሪያዎቹ ነገ ረቡዕ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም የሚካሄደውን የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ አስመልክተው በትላንትናው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም ከጥቅምት 27 እስከ ህዳር 6 ቀን 2012 ዓ.ም የተደረገው የመራጮች ምዝገባ ሠላማዊ ሆኖ መጠናቀቁ ተመላክቷል።

ስለሆነም መራጮች ምንም አይነት ስጋት ሳይገባቸው በነፃነት የፈለጉትን ምልክት እንዲመርጡ ጥሪ ተላልፏል።

የሲዳማ ዞን ሠላም እና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ፥ በዕለቱ የተለያዩ የመንግስት እና የንግድ ተቋማት አገልግሎት የማይሰጡ መሆኑን በማስታወስ መራጮች ያለምንም ስጋት ሙሉ መብታቸውን እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም ከዛሬ ማክሰኞ ምሽት12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ዓርብ ማለዳ ድረስ በሃዋሳ ከተማ እና የሲዳማ ዞን የሁለት እግር ሞተር ተሽከርካሪ አገልግሎት የተከለከለ መሆኑን ተናግረዋል።

የሀዋሳ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኮሎኔል ሮደሞ ኪኣ በበኩላቸው፥ ህብረተሰቡ በምርጫ ሂደቱ የፀጥታ ችግር ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ሰላምን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝ ጠይቀዋል።

ህዝበ ውሳኔዉን ተከትሎ ማንኛውም ህጋዊ ያልሆነ የድጋፍ እንዲሁም የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል።(ምንጭ ፋና)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top