Connect with us

በቦሌ ኤርፖርት 12 አደገኛ አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ዋለ

በቦሌ ኤርፖርት አደገኛ አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ዋለ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በቦሌ ኤርፖርት 12 አደገኛ አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ዋለ

መነሻውን ከብራዚል ሳኦፖሎ ያደረገ አደገኛ አደንዛዥ ዕፅ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET 507 በቀን 07/03/2012 ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በዓለም አቀፍ መንገኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በጉምሩክ ኢንተሊጀንስ ሰራተኞችና በኢንተር ፖል አባል እንዲሁም በሰዓቱ ከነበረ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል።

በሰዓቱም አደንዛዥ ዕፁን ሲያዘዋውር የነበረው ግለሰብ ባራቱንደ ሞጆድ የፓስፖርት ቁጥሩ 505538358 የሆነ አሜሪካዊ ቀጣይ የጉሾ መዳረሻውም ህንድ የነበረ ግለሰብ በሻንጣው ውስጥ ሻግ በመስራት 5.2 ኪሎ ግራም በገንዘብ 12 ሚሊዮን 64 ሺህ ብር የሚገመት ኮኬይን እንደያዘ በቁጥጥር ስር ውሏል።

አደንዛዥ ፅፁና አዘዋዋሪው መንገደኛው በቁጥጥር ስር የዋለው WCO-REGIONAL intelligence LIASON OFFICE (RILO)- EASTERN AND SOUTHERN AFRICA REGIONAL OFFICE በደረሰ መረጃና በተደረገ ክትትል ነው።

ህገ ወጥ ንግድና የኮንትሮባንድ ስራ የአገርን ሉዓላዊነት ለአደጋ የሚያጋልጥ፤ የማህበረሰቡን ማህበራዊ ህይወት የሚያቃዉስና የተረጋጋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዳይኖር የሚያደርግ በመሆኑ ህዝቡ እንደዚህ አይነት ህገ ወጦች ሲያጋጥሙ የሚያደርገዉን ጥቆማ አጠናክሮ ማስቀጠል አለበት ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top