ለ19ኛ ጊዜ የሚደረገው የ2012 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በ45 ሺ ተሳታፊዎች እና ከአምስት የተለያዩ ሀገራት በመጡ አትሌቶች አማካኝነት ነገ እሁድ ህዳር 7 ቀን 2012ዓ.ም በድምቀት ይከናወናል፡፡
የፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያን “ሴቶች ልጆች በእኩል ሊታዩ፤ ሊደመጡ እና ቦታ ሊሠጣቸው ይገባል” የሚለውን መሪ ቃል ያስተላልፋል፡፡
እንደሁልጊዜውም የዘንድሮም የውድድሩ የክብር እንግዳ በማድረግ ኬኒያዊቷን አትሌት ሄለን ኦቢሪን ጋብዟል፡፡
ኦቢሪ በ5000 ሜትር የሁለት ተከታታይ የአለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ እና በሪዮ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ እና የአንድ ልጅ እናት ናት፡፡
በቅርቡ ከአለም ምርጡ የጎዳና ላይ ውድድር ተብሎ እውቅና ያገኘው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ 45000 ተሳታፊዎቹን በጋራ የሚያንቀሳቅስ አስደሳች እና አዝናኝ የቡድን ዳንስ አዘጋጅቷል፡፡
በተጨማሪም በቀጣይ ዓመት የታላቁ ሩጫን ምስረታ 20ኛ ዓመት “አብረን 20 ዓመት” በሚል ርዕስ ይከበራል፡፡
የዚህ ክብረ በዓል አካል የሆነ የፎቶ አውደ ርዕይ እና ፎቶ መፅሔት ላይ የሚካተቱ ፎቶግራፎችን የማንሳት ውድድርም ተዘጋጅቷል፡፡
ለውድድሩ የተመዘገቡ ተሳታፊዎች ከህዳር 21 እስከ ታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ #20together ብለው የታላቁ ሩጫ
በኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ ገጽን በመጥቀስ ፎቶዎቻቸውን መለጠፍ ይኖርባቸዋል፡፡
ተሳታፊዎች በሩጫው ቀን ቀድም ብለው መግባት የሚገባቸው ሲሆን የአረንጓዴ ማዕበል ሯጮች በመነሻው ከ1፡00 ሰዓት በፊት መድረስ ያለባቸው ሲሆን የቄ ማእበል ተሳታፊዎችም በውድድሩ ቦታ ከሁሉት ሰዓት በፊት ቢደርሱ እንደሚመከር አዘጋጆቹ መክረዋል፡፡
ከታዋቂ አትሌቶች ውድድር ተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአምባሳደሮች ውድድር፤ የአካል ጉዳተኞች ውድድር እንዲሁ ዘንድሮ እንደ አዲስ የተጀመረው የተለያዩ ድርጅቶች የስራ አስኪያጆች ውድድር ለዝግጅቱ ጥሩ ቀለም እንደሚጨምሩለት ይጠበቃል፡፡
እንደ አለፉት አመታት ሁሉ የታላቁ ሩጫ ውድድሮችን ቅዳሜ በሚካሔደው የፕላን ኢንተርናሽናል የልጆች ውድድር ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የሚጀመር ይሆናል፡፡
የሩጫው ጠቅላላ መረጃ
የውድድሩ ቀን ሁለት የሻወር ጣቢያዎች ሲኖሩ ከውድድሩ መጨረሻ ከሚሰጠው አርኪ ውሃ በተጨማሪም በውድድሩ ግማሽ መንገድ ላይ የሚታደል መሆኑም ታውቋል፡፡
ዘጠኝ የሙዚቃ ጣቢያዎች፤ 20 የመጀመሪያ እርዳታ መስጪያ ጣቢያች 10 የአምቡላንስ መቆሚያዎች ከውድድሩ የህክምና ቢድን መሪ ዶር ሶፊያ ከበደ ጋር ተዘጋጅተው የሚጠብቁ ይሆናል፡፡
የመሮጫ መንገድ የዘንድሮ ታላቁ ሩጫ መነሻውና መድረሻው መስቀል አደባባይ ይሆናል፡፡
#የመነሻና #መድረሻ #ቦታ
የመሮጫ መስመሩም ከመስቀል አደባባይ ተነስቶ በስታድየም – ሜክሲኮ – ባልቻ ሆስፒታል – ጎማ ቁጠባ – ብሔራዊ አልኮል – ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ – ብሔራዊ ቴአትር – ሐራምቤ ሆቴል – ፍልውሃ – ቤተ መንግስት- ካዛንችስ – ዑራኤል – ባምቢስ – መጨረሻው መስቀል አደባባይ ነው፡፡
የዛሬው የህፃናቶቹ እርጫ መነሻውም መድረሻውም እዛው ለም ሆቴል እስፖርት አካዳሚ ነው።