በባህር ዳር እና አዲስ አበባ በከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ላይ የተፈፀሙት ጥቃቶች በብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ የተመራ መፈቅለ መንግስት ሙከራ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡
ዛሬ ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ/ም በተሰጠው መግለጫው እንደተገለጸው
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሰኔ 15 በአማራ ክልል ርዕሰ መስታዳድርና የስራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም በቀድሞ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ብርጋዴር ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የተፈፀመው ጥቃትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በአማራ ክልል ሰኔ 15 ቀን 2011 በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን ፣ እዘዝ ዋሴ እና ምግባሩ ከበደ ላይ የተፈፀመው ጥቃት በብርጋዴራል ጄኔራል አሳምነው ፅጌና ባልደረቦቻቻ ለመፈንቅለ መንግስት ተልዕኮ በተሰጣቸው አካላት የተፈፀመ መሆኑን በምርመራ ማረጋገጡን ጠቅላይ አቃቢ ህግ ብርሃኑ ፀጋዬ አስተውቀዋል፡፡
ብርሃዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ እና ለመፈንቅለ መንግስት ተልዕኮ በተሰጣቸው አካላት ከክልሉ ልዩ ሀይል የተውጣጡ ሰዎች በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፅህፈት ቤት ስብሰባ ላይ በነበሩት ዶክተር አምባቸው መኮንን በጥይት በመደብደብ ህይወታቸውን እንዲያልፍ አድርገዋል ብለዋል፡፡
እንዲሁም በአቶ እዘዝ ዋሴ ላይ በተመሳሳይ ጥቃት ህይወታቸውን እንዳለፈ የገለፁት ዐቃቢ ህጉ በወቅቱ ጥቃት የተፈፀመባቸው አቶ ምግባሩ ከበደም ህክምና ላይ በነበሩበት ወቅት ህይወታቸውን እንዳለፈ ገልፀዋል፡፡
ጉዳን በሰው እና የሰነድ መረጃ ማረጋገጥ እንደተቻለ ነው ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ የተናገሩት፡፡
በዚህ ጥቃት 15 ሰዎች ሞት ፣ በ20 ሰዎች ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ማጋጠሙን ተነግሯል፡፡
እንዲሁም ከዚህ ጥቃት ጋር በተያያዘ 114 ክለሽኮቭ ፣ ሶስት ብሬን እና ሌሎች መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለው የነበረ ሲሆን ከጥቃቱ ጋር ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸው መሳሪያዎች ተለይተዋል ብለዋል፡፡
ከተጠርጣሪዎቹ መኖሪያ ቤት ፣ መኪና ፣ ፍላሽ ዴስክ እና ኮሙፒውተሮች የተገኙ መረጃዎች በኤግዚቢትነት መያዛቸውን ጠቅላይ አቃቢ ህጉ ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ላይ በቀድሞ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ብርጋዴር ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና በጄኔራል ገዛሂ አበራ ላይ የተፈፀመው ጥቃት በብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ የተመራው መፈቅለ መንግስት ሙከራ አካል ነው ብለዋል፡፡
አለማው ብርጋዴር ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ግድያ ከተፈፀመ በኋላ ጥቃቱን ተከትሎ ወደ በስፍራው ይገኛሉ ተብሎ የተገመቱትን ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑን ጁላን በመግደል በሰራዊቱ ውስጥ መከፋፈል ለመፍጠር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በዚህም በባህር ዳር በከፍተኛ ስራ ሃላፊዎች ላይ ግድያው ከተፈፀመ ከሰዓታት በኋላ ብርጋዴር ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና አብረዋቸው በነበሩት ገዛዒ አበራ ላይ በግል ጠበቂያው ግድያ ሊፈፀም እንደቻለ ጸፀቁመዋል፡፡
ይህ ጥቃት ከሚያዚያ 2011 ጀምሮ ዝግጅት ሲደረግበት እንደነበረ በምርመራው መረጋገጡን የተናገሩት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ በብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ እና በአክቲቪስቶች ዝግጅት የተካሄደበት ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ጥቃት ጋር በተያያዘ በባህር ዳር 277 እንዲሁም 140 ተጠርጣሪዎች አዲስ አበባ ላይ በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበረ ተናግረዋል፡፡
በእነዚህ ላይ በተካሄደው ምርመራው ከባህርዳሩ 45ቱ የወንጀል ተሳትፎዋቸው አነስተኛ መሆኑን ተከትሎ በምስክርነት ተለይተዋል ተብሏል፡፡
ከአዲስ አበባዎቹ 140 ተጠርጣሪዎች 61ዱ በዋስትና መፈታታቸው የገለፁት ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ 5ቱ ደግሞ ከመፈንቅለ መንግስቱ መከራ ውጭ ከጦር መሳሪያ ዝውውር ጋር በተያያዘ ጉዳያቸው እንደተያዘ ተጠቁሟል፡፡
በአሁን ወቅት የሰነድና የሰው ማስረጃ የተጠናቀቀባቸው ከባህርዳር 55 እና ከአዲስ አበባ 23 ክስ ለመመስረት ዝግጅት መጠናቀቁን ዐቃቤ ህጉ ተናግረዋል፡፡