Connect with us

በሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ ለመስጠት ሁለት ሚሊዮን ገደማ መራጮች ተመዝግበዋል

በሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ ለመስጠት ሁለት ሚሊዮን ገደማ መራጮች ተመዝግበዋል
Photo: Facebook

ማህበራዊ

በሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ ለመስጠት ሁለት ሚሊዮን ገደማ መራጮች ተመዝግበዋል

ህዳር 10/2012 በሚካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ ለመስጠት ሁለት ሚሊዮን ገደማ መራጭ መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በተለይም በመጀመሪያዎቹ ቀናት ከፍተኛ የተመዝጋቢ ቁጥር የነበረ ሲሆን የምርጫ ጣቢያዎችም በተመዝጋቢዎች ተጨናንቀው ነበር፡፡

እስካሁን ምዝገባው ያለ አንዳች ችግር እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት ሶሊያና፤ በአንዳንድ ወረዳዎች የካርድ እጥረት አጋጥሞ የነበረ ሲሆን ካርድ በአፋጣኝ እንዲደርስ በማድረግ ችግሩ መቀረፉን ተናግረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ መሰረት የመራጮች ምዝገባ እስከ ህዳር 6/2012 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን የተመዝጋቢዎች ቁጥርም ከሁለት ነጥብ አንድ እስከ ሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

አዲስ ዘመን ህዳር 3/2012

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top