Connect with us

ከመቀሌ ወደ ባሕር ዳር የእግር ኳስ ግጥሚያ እንዲዛወር በካፍ ታዘዘ

ከመቀሌ ወደ ባሕር ዳር የእግር ኳስ ግጥሚያ እንዲዛወር በካፍ ታዘዘ
Photo: DW/A

ስፖርት

ከመቀሌ ወደ ባሕር ዳር የእግር ኳስ ግጥሚያ እንዲዛወር በካፍ ታዘዘ

የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፈደሬሽን (CAF) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ ከኮትዲቯር የሚያደርገውን ጨዋታ ከመቀሌ ወደ ባሕር ዳር እንዲያዛውር በደብዳቤ አሳሰበ።

ኢትዮጵያ የስታዲየሞቿን የጥራት ደረጃ ዝቅተኛውን መስፈርት ካላሻሻለች ቀጣይ ጨዋታዎችን መስፈርቱን በሚያሟሉ የኮንፌዴሬሽኑ አባል ሃገራት ውስጥ ለማከናወን እንደምትጠየቅ ካፍ አስጠንቅቋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በጊዜያዊነት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያካሂዱ ከተፈቀደላቸው ስታዲየሞች መካከል መቀሌ ስታዲየም ውስጥ ውድድር ማካሄድ እንደማይቻል ግን ካፍ ዐስታውቋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ ዶ/ር እያሱ መርኃጽድቅ የካፍ ማሳሰቢያ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ዛሬ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። ኾኖም ገምጋሚ ቡድኑ ይፋዊ በኾነ መልኩ ስለግምገማው ዝርዝር ዘገባ እንዳላቀረበላቸው ገልጠዋል። «ከዚህ ደብዳቤ ውጪ የላከልን ሪፖርት የለም» ብለዋል።

የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፈደሬሽን (CAF)ደብዳቤውን ለኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የላከው ከትናንት በስትያ ሰኞ ዕለት ነው። ስታዲየሞቹን ለመገምገም የተላኩት የካፍ ባለሞያ ከኢትዮጵያ ከመውጣታቸው በፊት ደብዳቤው እንደደረሳቸውም ዋና ጸሐፊው ተናግረዋል። «ትናንት ሌሊት ወይንም ዛሬ ንጋት ላይ ነው ወደ ሀገራቸው የሔዱት እና እንግዲህ ሪፖርታቸውን እዚህ ኾነው ልከውት ከኾነ ዐናውቅም» ሲሉ አክለዋል።

ካፍ በቅርብ ጊዜ መሻሻል ካልታየ ከእንግዲህ ውድድሮች ከኢትዮጵያ ውጪ ይደረጋሉ ማለቱን በተመለከተ ፌዴሬሽኑ ምን ሊያደርግ አስቧል ለተባለው ጥያቄ ዶ/ር እያሱ መርኃጽድቅ ሲመልሱ፥ ካፍ ዝርዝር መረጃዎችን ሲልክላቸው የዛኔ ዝርዝሩን እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል። ካፍ «ሦስቱን ስታዲየሞች ገምግሟል፤ ኾኖም ስለ ግምገማው ግን የላከልን መረጃ የለም» ብለዋል።

የአፍሪቃ እግር ኳስ ኮንፈደሬሽን (CAF)ኢትዮጵያ ውስጥ በሁለት ወራት ውስጥ ይሻሻሉ ሲል ምክረ-ሐሳብ እና ማስጠንቀቂያ ካቀረበ ሦስት ወራት ተቆጥረዋል። በነዚህ ጊዜያት ውስጥ የመቀሌ፣ የባሕር ዳር እና የወልዲያ ስታዲየሞች ይዞታቸው የካፍን መስፈርት አላሟሉም ብሏል። «ሦስቱን ስታዲየሞች ገምግሟል፤ ኾኖም ስለግምገማው የላከልን መረጃ ግን የለም» ብለዋል ዶ/ር እያሱ።

ካፍ በመሠረታዊ ደረጃ ስታዲየሞች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ዝቅተኛ መስፈርቶች ሲል ከሚዘረዝራቸው ነጥቦች መካከል፦የመልበሻ ክፍሎች፤ የመታጠቢያ ቤቶች፤ መጸዳጃ ክፍሎ፤ የመጫወቻ ሜዳዎች እና ሣሮች፤ እንዲሁም የጸጥታው ኹኔታ የሚሉት ይገኙበታል።

ምንጭ:- ዶይቸ ቬለ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top