Connect with us

ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ የኮሪያ ጦር ዘማቾች እንክብካቤ ማዕከል በአዲስ አበባ ገነባች

ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ የኮሪያ ጦር ዘማቾች እንክብካቤ ማዕከል በአዲስ አበባ ገነባች
Photo: Facebook

ባህልና ታሪክ

ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ የኮሪያ ጦር ዘማቾች እንክብካቤ ማዕከል በአዲስ አበባ ገነባች

ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ የኮሪያ ጦር ዘማቾች የእንክብካቤ ማዕከል በአዲስ አበባ መገንባቷን የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በ712∙8 ስኩዌር ሜትር መሬት ላይ ያረፈው ማእከሉ ባለ ሁለት ፎቅ ህንፃ እንደተገነባለትም በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ ተገልጿል።

እ.ኤ.አ. ከ1950 እስከ 53 በነበረው ጦርነት 3 ሺህ 500 እግረኛ ወታደሮቿን የላከችው ብቸኛ አፍሪካዊት ሀገር ኢትዮጵያ ነች፡፡

ከኢትዮጵያ ኮሪያ ከዘመቱት ወታደሮች ውስጥ 150ዎቹ አሁንም በህይወት ያሉ ሲሆን 122ቱ በጦርነቱ ሲሞቱ 536ቱ ደግሞ ቆስለዋል፡፡

ለአለም አቀፍ ወታደሮች ቁርጠኝነት እና መስዋዕትነት ምስጋና ለመግለጽ በኢትዮጵያ ውስጥ የተገነባው የበጎ አድራጎት ማዕከል በደቡብ ኮሪያ ሶስተኛው ፕሮጀክት ነው ተብሏል፡፡

እንዲህ ዓይነቱ የበጎ አድራጎት ማዕከል የመጀመሪያው የተገነባው እ.ኤ.አ. በ2014 በባንኮክ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በኮሎምቢያ ቦጎታ በ2017 መሆኑን መከላከያ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተቋሙ በሁለቱ አገራት መካከል የሚደረገውን የልምድ ልውውጥ ለማፋጠን መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል፡፡

በኮሪያ ጦርነት ወቅት የሰሜን ኮሪያ እና የቻይና ወታደሮችን ወረራ ለመከላከል 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ወታደሮች እና ከ3,000 በላይ አማካሪዎች ወደ ኮሪያ ባሕረ ሰላጤ መሬት እንደተላኩ የደቡብ ኮሪያ መንግስት መረጃ ያመለክታል፡፡

ከነዚህ ውስጥ 40,670 ያህሉ ሲገደሉ 104,280 ቆስለዋል እንዲሁም ከ 9000 በላይ የሚሆኑት አሁንም በህይወት ይገኛሉ ፡፡

ምንጭ፡- ዮፕ ኒውስ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top