Connect with us

የብሔራዊ ስታዲየም የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ሊጀመር ነው

የብሔራዊ ስታዲየም የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ሊጀመር ነው

ስፖርት

የብሔራዊ ስታዲየም የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ሊጀመር ነው

– ግንባታው 99 በመቶ ተጠናቋል ተብሏል፣

በ2 ነጥብ 47 ቢሊዮን ብር ወጪ በህዳር ወር 2008 ዓ.ም የተጀመረውና “አደይ አበባ” የሚል ስያሜ የተሰጠው የብሔራዊ ስታዲየም የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ ከአስር ቀናት በኋላ እንደሚጀመር የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ከ62 ሺህ በላይ ተመልካቾች የሚይዘው ይህ ስታዲየም የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ 99 በመቶ መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ስታዲየሙ ግንባታ ሲጀመር ከተያዘው ጊዜ ውጭ ተጨማሪ ስድስት ወራት ወስዶ አሁን 99 በመቶ ደርሷል ሲሉ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ናስር ለገሰ በተለይ ለኢቲቪ ገልጸዋል።

በቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን አማካኝነት እየተገነባ ያለው ፕሮጀክቱ 2 ቢሊዮን ክፍያ ለመጀመሪያው ምእራፍ ግንባታ መፈጸሙን ኃላፊው ተናግረዋል።

እንደ አቶ ናስር ገለፃ፣ ከውጪ የሚገቡ እቃዎች መዘግየት፣ የብረት ዋጋ መናር ፣የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲሁም ወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ የስታዲየሙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ይጠናቀቃል ከተባለበት ጊዜ ተጨማሪ ስድስት ወር አስፈልጎታል።

የአደይ አበባ ስታዲየም የሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ የጨረታ ሂደት 11 ወራትን ፈጅቷል ያሉት አቶ ናስር ጨረታው ሶስት ጊዜ ወጥቶ በመጨረሻ አሁን ላይ ስምምነት ተደርሷል ብለዋል።

በመጪዎቹ 10 ቀናት ውስጥ ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ይፋ ተደርጎ ወደ ስራ እንደሚገባም ነው የገለፁት፡፡

የስታዲየሙ ምእራፍ 2 ግንባታ የጣራ ስራ፣ የወንበር ገጠማ፣ የፊኒሺንግ፣ የሴኩሪቲ፣ የተለያዩ መሰረተ ልማት የማሟላት ስራዎች እንዲሁም ፓርኪንግ፣ የዋና ገንዳ እና ጂምናዚየም ሥራዎች ተካተውበታል።

ስታዲየሙ ለተለያዩ ሀገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶችን እንዲያስተናግድ 60 ሺ መቀመጫዎች እንዲኖረው ተደርጐ እየተገነባ ሲሆን ለከፍተኛ አመራሮች ፣ ለሚዲያ፣ ለስፖርተኞች፣ ለዳኞች እና ለክብር እንግዶች 2 ሺ ተጨማሪ መቀመጫዎች ስለሚሰሩ ብሔራዊ ስታዲየም 62 ሺ ተመልካቾች በድምሩ ማስተናገድ ይችላል ተብሏል።

ከስታዲየሙ ውጭ 3 ሺ 231 ተመልካች ማስተናገድ የሚችሉ ትናንሽ የእግር ኳስ ሜዳዎች እና የመሮጫ መም የሚኖረው ሲሆን 3 ሺ500 መኪናችን የማስተናገድ አቅም አለው።

የሂሊኮፕተር ማረፊያ፣ የቮሊቮል፣ የቅርጫት ኳስ፣ የባድሜንተን፣ የሜዳ ቴኒስ፣ አምፊቲያትር አዳራሾች፣ ሰው ሰራሽ ሀይቆች እና ፖርኮች እንዲሁም የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች የስታዲየሙ ውጫዊ ገፀ በረከቶች ናቸው ተብሏል።

ብሔራዊ ስታዲየሙ የአለም ዋንጫን እና የኦሎምፒክን መስፈርት ያሟላ ሲሆን ስታዲየሙ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ ኢትዮጵያ አህጉር አቀፍ እና አለም አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርላት ይጠበቃል።(ምንጭ፡- የባህልና ቱሪዝም ሚ/ር)

Click to comment

More in ስፖርት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top