Connect with us

በጆሐንስበርግ በወንጀለኞች ታግተው የነበሩ ሶስት ኢትዮዽያውያን ታዳጊዎች ተለቀቁ

በጆሐንስበርግ በወንጀለኞች ታግተው የነበሩ ሶስት ኢትዮዽያውያን ታዳጊዎች ተለቀቁ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በጆሐንስበርግ በወንጀለኞች ታግተው የነበሩ ሶስት ኢትዮዽያውያን ታዳጊዎች ተለቀቁ

በጆሐንስበርግ ከተማ ደቡብ አፍሪካ በወንጀለኞች ታግተው የነበሩ ሶስት ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች ተለቀው በፕሪቶሪያ ከተማ በሰላም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል፡፡

ታዳጊዎቹ ከወንጀለኞች ነፃ የወጡት በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከደቡብ አፍሪካ የጸጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የታዳጊዎቹ ወላጆችና ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከወንጀለኞች እጅ በሰላም መለቀቃቸው እጅግ እንዳስደሰታቸው የገለጹ ሲሆን፣ ኤምባሲው እና የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ላደረጉት ከፍተኛ ጥረትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ወንጀሉን የፈጸሙ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙም ኤምባሲው፤ ከታዳጊዎቹ ቤተሰቦችና ከህብረተሰቡ ጋር በጥምረት ይሰራል ተብሏል፡፡

በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር እንዲሁም በዜጎቻችን ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀለኞችን በህግ ለመፋረድ ለሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top