Connect with us

ዶክተር ወርቅነህ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ሆነው ተሾሙ

ዶክተር ወርቅነህ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ሆነው ተሾሙ
Photo: Facebook

ዜና

ዶክተር ወርቅነህ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ሆነው ተሾሙ

ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ጸሃፊ ሆነው ተሾሙ።

ዶክተር ወርቅነህ በትናንትናው ዕለት ተሰናባቹ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ አምባሳደር ኢንጂነር ማህቡብ ሟሊም፣ የኢጋድ አምባሳደሮች ሊቀ መንበር እና በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር አብዱላዚዝ መሃመድ በተገኙበት ስራ መጀመራቸውን ጅቡቲ ከሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዶ/ር ወርቅነህ ትናንት ከኢጋድ አባል አገራት ልዑካን ጋር ባወሩበት ወቅት ለቀጠናው የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ያላቸውን ፍላጎት የገለፁ ሲሆን ከሁለት ቀናት በፊትም ከጅቡቲ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሀመድ አሊ የሱፍ ጋር ተወያይተው ነበር።

ዶ/ር ወርቅነህ ከዚህ በፊት በተለያዩ ሚኒስቴር መ/ቤቶች በሚኒስትርነት ማገልገላቸው የሚታወስ ነው።

ምንጭ:- ኢ.ፕ.ድ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top