Connect with us

የጀዋር መሐመድን አካውንት ለማዘጋት በፌስቡክ ደጃፍ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠራ

የጀዋር መሐመድን አካውንት ለማዘጋት በፌስቡክ ደጃፍ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠራ
Photo: Worldatlas

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የጀዋር መሐመድን አካውንት ለማዘጋት በፌስቡክ ደጃፍ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠራ

አክቲቪስትና የሚዲያ ባለሃብቱን ጀዋር መሐመድ በቅርቡ ባደረገው ጥሪ መሠረት የግድያ ወንጀል የተፈጸመባቸውንና ጥቃት የደረሰባቸው ወገኖችን ፍትሕ እንዲያገኙ የሚጠይቁ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በነገው ዕለት በፌስቡክ ዋና መ/ቤት ደጃፍ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያካሂዱ አስታወቁ፡፡

አዘጋጆቹ እንዳሉት ነገ ጠዋት ( ከጠዋቱ ስምንት ሰዓት ) በፌስ ቡክ ዋና መ/ቤት በር ላይ የጃዋር መሐመድን ፌስ ቡክ ለማዘጋት፣ በፌስ ቡክ የተፃፃፋቸውን ወንጀሎች ለ አለም አቀፉ ፍርድ ቤት ለማቅረብ ፌስ ቡክ ትብብር እንዲያደርግ እና መሰል ጉዳዮች አስመልክቶ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። አዘጋጆቹ አያይዘውን ለኢትዮጽያውያን ወገኖች በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ካሊፎርኒያ በሜልኖ ፓርክ በመገኘት የትግሉ አካል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጀዋር መሐመድ ጠባቂዎቼ ሊነሱ ነው፣ ተከብቤያለሁ በሚል በፌስቡክ ያሰራጫቸውን መረጃዎች በማነበብ በቁጣ የተንቀሳቀሱ ደጋፊዎቹ በአዲስአበባ ዙሪያ፣ በአዳማ፣ በሐረር፣ በድሬደዋ፣ በአርሲ፣ በአምቦ…በሰዎችና በንብረት ላይ አሰቃቂ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን ጠ;ሚኒስትር ዐብይ በገለጹት መሠረት ለ86 ኢትዮጽያውያን ወገኖች በግፍ ሞት መንስኤ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

ይህን ወንጀል ተከትሎም አጥፊዎች ከላይ አስከታች በሕግ እንዲጠየቁ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚደረገው ጫና ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ሰሞኑንም ዕውቁ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ከዚሁ የግፍ ግድያ ጋር በተያያዘ ፌስቡክን ለመክሰስ መወሰኑን መናገሩ የሚታወስ ነው፡፡

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top