Connect with us

ቃሉ በአንበጣ መንጋ ጭንቅ ውስጥ ናት!

ቃሉ በአንበጣ መንጋ ጭንቅ ውስጥ ናት!
Photo: Facebook

ዜና

ቃሉ በአንበጣ መንጋ ጭንቅ ውስጥ ናት!

ቃሉ በአንበጣ መንጋ ጭንቅ ውስጥ ናት! መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ይስጥ !
(ኃይሌ ተስፋዬ በድሬ ቲዩብ)

በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ በደጋን ና አካባቢው የአንበጣ መንጋ ተከስቶ በማሽላ ና በእንስሳት መኖ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ከአሁን በፊት በወጡ መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል።

ይሁንና ይህንን የአንበጣ መንጋ በባህላዊ መንገድ ለመከላከል አርሶ አደሮች፣ ተማሪዎች፣ የልዩ ኃይል አባላት፣ ወጣቶችና የአካባቢው ማኅበረሰብ በጋራ በመሆን ለማስወገድ የተቻላቸውን ያህል ርብርብ ቢያደርጉም የአንበጣ መንጋው በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

ከፍ ያለ ጉዳት ከደረሰባቸው ቀበሌዎችም ውስጥ ከግራር አንባ ቀበሌ ጨለቃ ወንዝን ተከትሎ በ018 አባ ህልሜ፣ 021 አራቦ፣ 022 ወዳጆ፣ 019 አበቾና አካባቢው ጥቂቶቹ ይገኙበታል።

ይህ ጉዳት ከፍተኛ ከመሆኑም የተነሳ ዛሬ ማለትም 26/2/12 ዓ.ም የአንበጣ መንጋውን ለመከላከልና የደረሰውን ሰብል መሰብሰብ ይቻል ዘንድ፥ በሀርቡ ከተማ ለሚገኙ ወጣቶችና የኅብረተሰብ አካላት ወደ እነዚህ ቀበሌዎች በማምራት የዘመቻውን ስራ ይቀላቀሉ ዘንድ በቀበሌው አስተዳደር ጥሪ ተላልፏል።

ይሁንና ይህ ጉዳት በእነዚህ በተጠቀሱት ቀበሌዎች ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አጎራባች ቀበሌዎች እየተስፋፋ ስለሚገኝ፥ ከወረዳ በዘለለ የዞን አስተዳደር አካላት ትኩረት ሰጥተው የተቀናጀና በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት ማድረግ ይቻል ዘንድ የመፍትሄ አካል ይሆኑ ዘንድ በስልክ ያነጋገርኳቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top