Connect with us

ለያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ጨረታ አንድ ኩባንያ ብቻ መቅረቡ ተገለጸ

ለያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ጨረታ አንድ ኩባንያ ብቻ መቅረቡ ተገለጸ

ኢኮኖሚ

ለያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ጨረታ አንድ ኩባንያ ብቻ መቅረቡ ተገለጸ

በየዓመቱ አንድ ነጥብ 592 ቢሊዮን ብር ዕዳና ወለድ ክፍያ ይጠበቅበታል

አዲስ አበባ፡- የያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ በሽርክና ግንባታውን አጠናቆ ወደ ምርት ለማስገባት ባወጣው ጨረታ ሰነድ ያስገባው አንድ ድርጅት ብቻ መሆኑን፤ እስካሁን ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ወለድ መክፈሉንና በየዓመቱ አንድ ነጥብ 592 ቢሊዮን ብር ዕዳና ወለድ መክፈል እንደሚጠበቅበት ኮርፖሬሽኑ ገለጸ።

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የፕሮጀክት ጥናትና ትግበራ ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ዋለልኝ ለፋብሪካው ግንባታ ከባንክ 10ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ብድር ወስዶ ለብረታ ብረትና ኢንጅነሪግ ኮርፖሬሽን አምስት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር መክፈሉን ፤ ብድሩ ከተወሰደበት ጊዜ ጀምሮም ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ወለድ መከፈሉን ገልፀዋል።

‹‹ከሐምሌ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በየሶሰት ወሩ 398 ሚሊዮን ብር ለዕዳና ለወለዱ መከፈል ነበረበት›› ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ኮርፖሬሽኑ ገንዘብ ስለሌለው የሁለት ጊዜ ክፍያ 796 ሚሊዮን ብር ዕዳ መክፈል እንዳልቻለ፣ በ2012 ዓ.ም በአራት ጊዜ ክፍያ አንድ ነጥብ 592 ቢሊዮን ብር ዕዳ መክፈል እንደሚኖርበት አመልክተዋል።

የያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ ዕዳን በሙሉ ለመክፈል 11 ዓመታትን የሚወስድ በመሆኑ ኮርፖሬሽኑ ዕዳውን ለመክፈል ስለማይችል መንግስት ማስተካከያ ካላደረገ በህልውናው ላይ አደጋ እንደሚያስከትል፤ የኮርፖሬሽኑን ካፒታልም ሊጨርስ እንደሚችል ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

ዳይሬክተሩ ‹‹በከሰል የሚሰራ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት በጋዝ ከሚሰራው ፋብሪካ እስከ 150 በመቶ ጭማሪ አለው። በዚህ ላይ የአካባቢ ብክለት ያስከትላል። በዓለም ላይ በድንጋይ ከሰል ማዳበሪያ የሚመረተው በቻይና ብቻ ነው።

በድንጋይ ከሰል የሚሰራ የማዳበሪያ ፋብሪካ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን በዓመት ከ600ሺ ቶን በላይ ማምረት አለበት። የያዮ ማዳበሪያ ፋብሪካ በዓመት ሊያመርት የታሰበው 300ሺ ቶን ብቻ በመሆኑ፤ ኮርፖሬሽኑ ፋብሪካው በገበያ አዋጭ አለመሆኑንና ከውጭ አገር ከሚገባው ጋር መወዳደር እንደማይቻል ባለን እውቀትና ሃላፊነት ለመንግስት በማቅረብ የማስረዳት ሃላፊነታችንን ተወጥተናል›› ይላሉ።

ዳይሬክተሩ ‹‹መንግስት ፋብሪካውን ከብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በመንጠቅ የቀረውን ስራ የግል ባለሀብቶች በሽርክና እንዲያከናውኑ ውሳኔ በማሳለፉ ወሳኔውን ተከትሎ ከሰባት ወር በፊት በጋራ ለማልማት ፍላጎት ያላቸው ባለሀብቶች በማስታወቂያ ተጋብዘው ሰባት ድርጅቶች ፍላጎታቸውን ያሳዩ ቢሆንም ከሰባቱ ብቃት ያላቸው ሶስቱ መሆናቸው ተለይቷል።

ሶስቱ ኩባንያዎች የቴክኒክ፣ የትግበራና የፋይናንስ እቅዳቸውን ለኮርፖሬሽኑ እንዲያቀርቡ ጊዜ በመወሰን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመናል። የተቀመጠው ጊዜ አነሰን በማለታቸው ጊዜ ተራዝሟል። ባለፈው ዓርብ የጨረታው የመጨረሻ ቀን ሲሆን ከሶስቱ ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ ያስገባው አንድ ድርጅት ብቻ ነው›› ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የጨረታ ህግ ቢያንስ ሶስት ድርጅቶች መወዳደር እንደሚገባቸው፤ የኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባላት የአንዱ ድርጅት ሰነድ እንደሚከፈት፣ የአተገባበር፣ የቴክኒክና የፋይናንስ እቅዱን በመገምገም መንግስት የሚፈልገውን የሚያሟላ መሆኑንና አለመሆኑን በመመዘን መንግስት የሚፈልገው አይነት ከሆነ አብሮ መሥራት እንደሚቻል፣ ይህ ካልሆነ ግን የፕሮጀክቱ ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

አዲስ ዘመን ጥቅምት 26/2012

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top