Connect with us

የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ስካውቶች ሌሊቱን ከእሳት ጋር ሲፋለሙ አደሩ

የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ስካውቶች ሌሊቱን ከእሳት ጋር ሲፋለሙ አደሩ

ዜና

የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ስካውቶች ሌሊቱን ከእሳት ጋር ሲፋለሙ አደሩ

የአፍሪካ ዝኆኖች መጠለያ የሆነው ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ለመከላከል ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡
የብሔራዊ ፓርኩ ስካውቶች ሌሊቱን ከእሳት ጋር ሲፋለሙ አድረዋል፡፡
****
ከሄኖክ ስዩም

ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ የምተማመንበት የሀገሬ የተፈጥሮ መስህብ ነው፡፡ እንደ ዘመነው የአፍሪቃ ፓርክ ከመኪና ሳልወርድ ዝኆን ሲንጎማለል የተመለከትኩበት ብሔራዊ ፓርክ ነው፡፡ ከአጋዘን ጋር አብረን የተጓዝንበት ቅርስ ነው፡፡ ብዙ ተስፋ ያደረኩትን መስህብ በተመለከተ ትናንት ጋዜጠኛ ፍሬወይኒ ደውላ ቃጠሎ ላይ መሆኑን ነገረቺኝ፤ ሳልተኛ አደርኩ፡፡ ሳይተኙ ያደሩት የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ስካውቶች እሳቱን ሲፋለሙ አንግተዋል፡፡ እሳቱን የመቆጣጠር ተስፋ ፈንጥቋል፡፡

ዘነበ የብሔራዊ ፓርኩ ሃላፊ ነው፡፡ ስለ ቃጠሎ ስጠይቀው በተጎዳ ስሜት ማታ አረጋገጠልኝ፡፡ ወርቅ የሆነው ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ሌላ ወርቅ ካላወጣን የሚሉ ህገ ወጦች የለኮሱት እሳት ከሺ በላይ ሄክታር ምድር አጥፍቷል፡፡መከላከያና ልዩ ሃይል መግባቱን ሰምቻለሁ፡፡ ከአርባ በላይ የፓርኩ ጠባቂዎች አንግተው ለብሔራዊ ፓርኩ ስቃይ እረፍት ሆነዋል፡፡

ከባድ እሳት ቢሆንም ከባድ ቁርጠኝነት አርፎበት እጅ እየሰጠ ነው፡፡ ዛሬ ጠንክረው ከዋሉበት ቃፍታን ከውድመት መታደግ ይቻላል፡፡ አሁን ተስፋ አለ፤ የሚመለከተው ሁሉ ዓይኑን ከብሔራዊ ፓርኩ ላይ ማንሳት የለበትም፡፡ የክልሉ መንግስት አንድ ለእናቱ የሆነውን ብሔራዊ ፓርክ አለኝታ በመሆን ይታወቃል፡፡ የህገ ወጥ እሳት ጫሪዎችን ጉዳይ በአስቸኳይ እልባት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ብቻውን ወርቅ ነው፡፡ እሳት ለሚበላው ወርቅ ሳንባ የሆነውን ተፈጥሮ በእሳት ማስበላት አይጠቅምም፡፡

ትኩረት ለቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ፤

Back Story 

ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ-ተከዜ ዳርቻ ነን

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ እያቀናሁ ነው ሲል ትረካውን ጀምሯል፡፡ ጉብኝቱ የሰሜን ብሔራዊ ፓርኮች ይዳስሳል፡፡ ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ይህ ነው ሲል እንዲህ ያስጎበኘናል፡፡)

(ሔኖክ ስዮም በድሬትዩብ)
==============
ብዙ ከተማ ዘልያለሁ፡፡ ለትረካው ተጣድፌ ነው፡፡ ውበትና ህይወት፣ በርሃና ተፈጥሮ አጣደፉኝ፡፡ ከጉዞዬ መልስ ከወልዲያ እስከ ሽሬ መንገድና ጉዞን እንዲህ ነው ልላችሁ ቃል እገባለሁ፡፡ አሁን ተከዜ ወንዝ ዳርቻ ነኝ፡፡ የሞላው ተከዜ ያለድምጥ ከሚሄድበት ልዩ ስፍራ፤ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የሰሜኑ የሀገራችንን ፓርኮች ተዋወቋቸው ሲል ጋዜጠኞች ይዞ እየዞረ ነው፡፡ ዛሬ ይህ ጉዞ ቃፍታ ሽራሮ ገብቷል፡፡

ተከዜ ዳርቻ የጎረቤት ሀገር በረኽኞች ውሃ በአህያ ከሚቀዱበት ታላቁ ወንዝ ስር ነኝ፡፡ ቃፍታ ሽራሮ ተከዜ ሸለቆ ውስጥ የሚገኝ የእጣን ዛፍ መዓዛን እየማገ የሚኖር የዝሆኖች መኖሪያ ነው፡፡ አሁን ያለሁባት ስፍራ እንዳመቐ ትባላለች፡፡ የጎብኚዎች ማረፊያ ካምፕ ናት፡፡ ጀበል ኡስማን ተራራ በቀኜ አለ፤ ኽለጊን በግራዬ ነው፡፡ መሀላቸው ከተጣለ ድንኳን አዞዎች ጸሐይ ከሚሞቁበት ዳርቻ ነኝ፡፡

ተከዜ ትልቁ ወንዝ ነው፡፡ ወንድማማቾቹን ነጥሎ ገላውን ሳይቀር ተካፍለው ድንበር ያደረጉት፤ አእዋፍ ይዘምራሉ፡፡ ዝሆን የገነደሳቸው ዛፎች ወዳድቀዋል፡፡ ሙቀቱ ዛፍ ስር ያለሁ እስካይመስለኝ ይፈታተነኛል፡፡ እንዲያም ሆኖ ዘለዓለም ላይረሳ ከሚችል ድንቅ ስፍራ ነኝ፡፡

መሀል አዲስ አበባን አሰብኳት እኔ በመቐለ ስለመጣሁ 1400 ኪሎ ሜትር ተጉዣለሁ፡፡ በ1999 ዓ.ም. የተመሰረተው ፓርክ ከጎረቤት ሀገር ኮረብታዎች ጋር የተፋጠጠ ነው፡፡ አሁን ፊት ለፊቴ ቆጨሮ ተራራ እያየሁ ነው፡፡ ገብረ እግዚአብሔር አብረሃ የቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ዋርደን ነው፡፡ ስለ አለሁበት ቦታ ነገረኝ፡፡

የኤርትራዋ አሞናሀጅር ከተማ አቅራቢያ ነን፡፡ በቅርቡ በሰፈራ ተከዜ ዳርቻ የወረዱት ኤርትራውያን አዲስ መንደር መስርተዋል፡፡ 2174 ስኩዌር ካሬ ሜትር የቆዳ ስፋት የሚሸፍነው ብሔራዊ ፓርክ በትግራይ ክልል የሚገኝ ብቸኛው ብሔራዊ ፓርክ ሆኖ የተመዘገበ ነው፡፡

የሜዳ ፍየልና የቆላ አጋዘንን የመሰሉ ዱር እንስሳት ቢኖሩበትም ጉልበተኛው ዝሆን እንደልቡ ይራወጥበታል፡፡ አእዋፍ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው፡፡ ጸሐይዋ ገብታለች፡፡ ወደ ሌላኛው የፓርኩ ክፍል የተጓዙት ዝሆኖች የተከዜ ዳር አዳራችን ስጋት እንደማይሆኑ ተነግሮናል፡፡ አስፈሪ የእባብ ዝርያዎች የሚገኙበት ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ ከምንም ስጋት ነጻ የሆነ ይሄንን የመሰለ ካምፕ ሳይት አለው፡፡ ያም ቢሆን የዱር ውስጥ አዳር እንደ አልቤርጎ በቀላሉ አይለመድም፡፡ እስኪነጋ ቸኩያለሁ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top