Connect with us

በ2018 ብቻ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች በኤችአይቪ ተጠቅተዋል

በ2018 ብቻ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች በኤችአይቪ ተጠቅተዋል

ጤና

በ2018 ብቻ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች በኤችአይቪ ተጠቅተዋል

ባለፈው የፈረንጆች 2018 ብቻ በመላው አለም የሚገኙ 1.7 ሚሊዮን ያህል ሰዎች በኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ ተጠቂ መሆናቸውን ፖለቲኮ ድረገጽ ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ አመልክቷል፡፡

ባለፈው አመት ከኤችአይቪ ኤድስ ጋር በተያያዘ ለህልፈተ ህይወት የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር ከ770 ሺህ በላይ እንደሚደርስ የጠቆመው ዘገባው፣ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ከሚገኙት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው አገራት ዜጎች መሆናቸውንም ገልጧል፡፡

ለቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ከሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ሴቶች ቀዳሚነቱን እንደሚይዙ የጠቆመው ዘገባው፣ በአለማችን በየሳምንቱ ከ15 እስከ 24 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 6ሺህ ያህል ሴቶች በቫይረሱ እንደሚጠቁም አመልክቷል፡፡

ባለፉት 8 አመታት በኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ የሚጠቁ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ያደገባት ቀዳሚዋ የአለማችን አገር ፊሊፒንስ መሆኗን የጠቆመው ዘገባው፣ በቫይረሱ የተያዙ የአገሪቱ ዜጎች ቁጥር በ203 በመቶ መጨመሩንም ገልጧል፡፡
ግብጽ በ196 በመቶ ጭማሪ የሁለተኛነት ደረጃን ስትይዝ፣ ማዳጋስካር በ193 በመቶ በሶስተኛነት እንደምትከተልም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ የተጠቁ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰባት ቀዳሚዋ የአለማችን አገር ኮሞሮስ መሆኗንና በአገሪቱ የ67 በመቶ ቅናሽ መታየቱንም አክሎ ገልጧል፡፡

በሲንጋፖር የ66 በመቶ፣ በቬትናም የ64 በመቶ፣ በካምቦዲያ የ62 በመቶ፣ በሩዋንዳ የ61 በመቶ፣ በታይላንድ የ59 በመቶ፣ በኔፓል የ57 በመቶ ቅናሽ መታየቱንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

ምንጭ:- አዲስ አድማስ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top