Connect with us

ልብ ልንላቸው የሚገቡ የልብ ህመም ምልክቶች….

ልብ ልንላቸው የሚገቡ የልብ ህመም ምልክቶች….
Photo: Health line

ጤና

ልብ ልንላቸው የሚገቡ የልብ ህመም ምልክቶች….

በዓለማችን በሰዎች ላይ በከፍተኛ ደረጃ ሞትን ከሚያስከትሉ በሽታዎች ውስጥ የልብ ህመም ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።

በድንገት ሞት በማስከተል የሚታወቀው የልብ ህመም በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት በመቅጠፍም ነው የሚታወቀው።

የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመላክተው በየዓመቱ 17 ነጥብ 9 ሚሊየን ሰዎች በልብ ህመም እና ከልብ ህመም ጋር ተያይዘው በሚከሰቱ የጤና እክሎች ህይወታቸውን ያጣሉ።

አብዛኛው ሞቶችም በዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ላይ በስፋት የሚከሰት ሲሆን፥ ለልብ ህመም ህክምናም ዓለማችን በየዓመቱ በቢሊየን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ታወጣለች።

የልብ ህመም በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት፣ ከልክ ያለፈ ውፍረት፣ ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል መጠን በሰውነታችን ውስጥ መብዛት፣ ሲጋራ ማጨስ እና ተያያዥ ምክንያቶች ተጠቃሽ ናቸው።

የልብ ህመምን ቀድሞ በሚታዩ ምልክቶች አማካኝነት በመለየትም ተገቢውን ህክምና ካገኘት የሚያስከትለውን የሞት መጠን መቀነስ አንደሚቻልን ነው የተነገረው።

እኛም ዛሬ ስለ ልብ ህመም ምልክቶች በጥቂቱ ልናካፍላችሁ ወደድን፤ የሚከተሉት ምልክቶች የድንገተኛ የልብ ህመም ምልክቶች ስለሆኑ ልብ ብንላቸው መልካም ነው።

እነሱም፦

* የደረት ህመም፥ ተመሳሳይ የህመም ስሜት ትከሻ እና አንገት ላይ አንገት ላይ ይሰማዎታል።

* ትንፋሽ ማጠር

*ማስመለስ/ማቅለሽለሽ

*በድንገት ማላብ

*አቅም ማጣት

እነዚህ ምልክቶች ከተሰማዎ ባፋጣኝ በአቅራቢያ ወዳለው ጤና ተቋም መሄድ ተገቢውን ህክምና ማድረግ መልካም ነው።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top