Connect with us

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ተከሰው የነበሩ ተከሳሾች ተፈረደባቸው

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ተከሰው የነበሩ ተከሳሾች ተፈረደባቸው
Photo: Facebook

ማህበራዊ

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ተከሰው የነበሩ ተከሳሾች ተፈረደባቸው

ነሀሴ 28 2008 ዓም የቂሊንጦን ማረሚያ አቃጥላችኃል ተብለው ተከሰው ከነበሩ 38 ተከሳሾች ውስጥ የቀሩት 4 ተከሳሾች ጥቅምት 18 ቀን ዓ. ም ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ የቅጣት ውሳኔው በማረሚያ ቤት ጉዳይ አስፈጻሚ በኩል ተላከላቸው፡፡ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ 4ኛ ወንጀል ችሎት ክሳቸውን ሲከታተሉ የነበሩት 4 ተከሳሾች 31ኛ ተከሳሽ ጌታቸር እሸቴ 32ኛ ቶፊቅ ሽኩር 33ኛ ፍፁም ጌታቸው 34ኛ ሸምሱ ሰይድ ወደ ችሎት ሳይመጡ ቅጣት ፎባቸዋል።

31ኛ እና 33ኛ ተከሳሾች ጌታቸር እሸቴ እና ፍፁም ጌታቸው 11አመት ቅጣት ሲተላለፍባቸው 32ኛ እና 34ኛ ተከሳሾች ቶፊቅ ሽኩር እና ሸምሱ ሰይድ 12 አመት እስራት ተላልፎባቸዋል፡፡

ቤተሰብ በዳኞች ቢሮ በኩል እስረኞች ለምን እዳልመጡ ሲጠይቁ ዳኞች ለታራሚዎች ደህንነት ሲባል እስረኞች እንዳይመጡ የተደረገው ምክንቱ ቅጣቱን ሲሰሙ ስሜታዊ ይሆኑና ከፖሊስ ጋር ግጭት ይፈጥራሉ ስለዚህ ለደህንነታቸው ሲባል ውሳኔው እዛው እንዲደርሳቸው የተደረገው ብለዋል ፡፡

ዳኞች ለቤተሰብ ቅጣቱን በቢሮ ያነበቡ ሲሆን ተከሳሶች ጥፋተኛ በተባሉበት በወንጀል ህጉ አንቀጽ 540 እና 464 (ለ) እርከን 30 ስር ያረፈ ሲሆን በወንጀል ህጉ አንቀጽ 540 ከ5 አመት እስከ 20 አመት የሚያስቀጣ ሲሆን በወንጀል ህጉ አንቀጽ 464 (ለ) ከ5 አመት ያልበለጠ ቅጣት ያስቀጣል ይህንን አመዛዝነን ነው የወሰነው ያሉ ሲሆን ተከሳሾች ይህን ድርጊት ፈጽመው እጃቸው ከተያዙበት ቀን ጀምሮ ፍርዱ ታሳቢ የሚሆን ሲሆን ይግባኝ ማለት ይቻላል ፡፡

ተከሳሾች ምንም አይነት ማቅለያ ያላቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የራሱን ቅጣት ማቅለያ ለተከሳሾች የሰጠ ሲሆን ጌታቸር እሸቴ እና ፍፁም ጌታቸው 2 ማቅለያ የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን እና ወንጀል ሪከርድ እንደሌለባቸው በማቅለያነት ተዞይላቸዋል፡፡ ቶፊቅ ሽኩር እና ሸምሱ ሰይድ አንድ የቅጣት ማቅለያ ወንጀል ሪከርድ እንደሌለባቸው ተዞይላቸዋል፡፡

ምንጭ:- ዋዜማ ራዲዮ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top