Connect with us

ሙስና ሲቀበል የነበረው ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ

ሙስና ሲቀበል የነበረው ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ሙስና ሲቀበል የነበረው ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ

3 መቶ ሺ ብር ሙስና ሲቀበል የነበረው ግለሰብ በፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ ተያዘ፡፡

ድርጊቱ የተፈፀመው ጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ይርጋ ሃይሌ ገበያ ማዕከል 3ኛ ፎቅ ሉሲ ካፌ ውስጥ ነው፡፡

ተጠርጣሪው የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ገቢዎችና ጉሙሩክ ኢንትለጀንስ ሰራተኛ ሲሆን የማይገባውን ጥቅም ለራሱ ለማግኘት በማሰብ ግብር ከፋይ ከሆነችው የግል ተበዳይ 3 መቶ ሺ ብር ሲቀበል በፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ መያዙን የክ/ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ሃላፊ ኮ/ር ጌታነህ በቀለ ተናግረዋል፡፡

የጉዳዩ መርማሪ የሆኑት ኢ/ር ጎይቶም ሃለፎም እንደተናገሩት ተጠርጣሪው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲል የግል ተበዳይን የ2007 እና የ2008 ዓ/ም የግብር ደረሰኝ የከፈለችበት ስህተት ስላለበት ይህ ደግሞ በወንጀል ስለሚያስጠይቅሽ እኔ ላስተካከልልሽ እችላሉ በማለት ከቀጠራት በኋላ ይዛለት የመጣችውን ገንዘብ ተቀብሎ ለመሄድ ሲሞክር በፖሊስ አባላት ከ3 መቶ ሺ ብር ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዞ ጉዳዩ በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ መግለፃውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያትታል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top