Connect with us

ሀበሻት ስድብ የመሰላችሁን ሳይኾን ለሀበሻ ክብር የተዋደቁትን አባቶቻችሁን …

ሀበሻት ስድብ የመሰላችሁን ሳይኾን ለሀበሻ ክብር የተዋደቁትን አባቶቻችሁን ...
Photo: Facebook

ፓለቲካ

ሀበሻት ስድብ የመሰላችሁን ሳይኾን ለሀበሻ ክብር የተዋደቁትን አባቶቻችሁን …

ሀበሻት ስድብ የመሰላችሁን ሳይኾን ለሀበሻ ክብር የተዋደቁትን አባቶቻችሁን ስናስብ አምቦ ዛሬም የደም ገንቦ ክብራችን ናት፡፡
****
ከስናፍቅሽ አዲስ

ሀበሻነት ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎ በዓለም ስሙ የገነነ የምስራቃዊ አፍሪካ ሀገር ህዝቦች ሌላ መገለጫ ነው፡፡ ሀበሻ ዳር ድንበሩ እንዲከበር፤ ሀበሻ ክብሩ ከፍ እንዲል፣ ሀበሻ ስሙ እንዲናኝ፣ ሀበሻ የወንዶች ሀገር ነው እንዲባል ያደረጉ ጀግኖችን እንቁጠር ካልን አምቦ ያፈራቻቸው የሸዋ ጀግኖች ብቻ መዝገብ አይበቃቸውም፡፡

ምዕራብ ሸዋ የአርበኞች ሀገር ነው፡፡ የቅዱሳን ሀገር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ አስኳል ምድር ነው፡፡ እናም የአምቦን ሰው ከኢትዮጵያ ነጥሎ ማየት አይቻልም፡፡ የአምቦ ሰው ሲባል ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት አንዳች ነገሩን ሳይሰስት በኢትዮጵያ ተራሮች የቀረ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመሳደብ የተመረጠው ቃል ሀበሻ የሚለው መሆኑ አስገርሞኛል፡፡ ሀበሻነት ምን እንደሆነ ለሀገር ሲዋደቁ ጊዜ አጥተው ያልተናገሩ አባቶች የወለዷቸው ልጆች ለምን ታላላቆቻቸው ዋጋ እንደከፈሉ አላወቁም፡፡

አምቦ ሀበሻ የሚኮራባቸው የትልልቆቹ ሀገር ናት፡፡ የኩራት መገለጫዎቻችን የትውልድ ቀዬ በመሆኗም ስሟ ገናና ነው፡፡ የአምቦ ፍሬዎች በሀበሻነታቸው የሚኮሩ ሴምን ከኩሽ ጋር ያዋሃዱ፤ አክሱም ከገዳ ያስማሙ ጎንደርን ከኦዳ ያስታረቁ ልሂቃን ሀገር ናት፡፡ የማንነት ቀውስ ያልደረሰባት አምቦ ዛሬም የደም ገንቦ መልከ መልካም ምድር፤

በሀበሻ ሥነ- ጽሑፍ ትልቁ ሰው ሎሪት ጸጋዬ ገብረመድህን ነው፡፡ የሎሪቱን ያክል አፋን ኦሮሞን ጠንቅቆ የሚያውቅ የኦሮሚኛ ፎክሎር ሩቅ ድረስ ጠንቅቆ የተረዳ ሌላ ሰው መጥራት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ አምቦ የታላላቆቹ ሀገር ናት፡፡ የታላላቆቹ ልጆች ትንሽ ስህተት ሰሩ፤ ሀበሻነት ስድብ መሰላቸው፡፡ የአባቶቻቸው ገድል ግን የአለማወቅ ሐጢአታቸውን ማንጻት የሚችል ነው፡፡ እናም ዛሬም እንደትናንቱ ለአምቦ ክብር አለን፤ ለአምቦ ወጣቶችም፤

ለሀበሻነት በተከፈለ ዋጋ የአምቦ ልጆች የከፈሉት መስዕዋትነት በኢትዮጵያ ታሪክ በማይጠፋ ብዕር የተጻፈ ትልቅ እውነት ነው፡፡ ይህንን እውነት የአንድ ቀን ሆታ አያጠፋውም፡፡ የአምቦ ልጆች የባንዳ ልጆች አይደሉም፡፡ የአምቦ ልጆች የደማቁ የኢትዮጵያ የነጻነት ታሪክ ባለድርሻዎች ፍሬ ናቸው፡፡

አምቦ እንዲህ ባለው ቃል ቅሬታዋን ስትገልጽ መስማት ቅር ቢያሰኝም የመታረም እድል ያለው ነው፡፡ አምቦ የደም ገንቦ ከመሆን የሚያግዳት የታሪክ መሰረት የለም፡፡ አምቦ የሀበሻ መገለጫ ዘብ የሆኑ ጀግኖች የተፈጠሩባት የኩራታችን ምድር ናት፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top