Connect with us

ሞባይል ለመስረቅ ሲል የሰው ነፍስ ያጠፋው በ20 ዓመት እስራት ተቀጣ

ሞባይል ለመስረቅ ሲል የሰው ነፍስ ያጠፋው በ20 ዓመት እስራት ተቀጣ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ሞባይል ለመስረቅ ሲል የሰው ነፍስ ያጠፋው በ20 ዓመት እስራት ተቀጣ

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በውንብድና ወንጅል የሰው ነፍስ ያጠፋው ተከሳሽ ባዬ አዱኛ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በጽኑ እስራት ተቀጣ::

ተከሳሽ የወንጅል ሕግ አንቀፅ 671/2 ላይ የተመለከተዉን በመተላለፍ የማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ቦታው ወታደር ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሟች የወ/ሮ በድሪያን ሞባይል ሲወስድ ከሟች የገጠመውን ተቃውሞ ለማስቀረት ሲል ነውረኝነቱንና ጨካኝነቱን በሚያሳይ ሁኔታ በያዘው ስለት ሟችን አንገቷ ሰር በመውጋት ባደረሰባት ጉዳት ምክንያት በተፈጠረባት የመተንፈሻ አካል ጉዳት ህይወቷ ያለፈ በመሆኑ ተከሳሽ በፈፀመው ከባድ ውንብድና ወንጅል መከሰሱን የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡

ዐቃቤ ሕግ በምርምራ መዝገቡ መሰረት የሰዉ፣ የሰነድ እና ገላጭ በሆነ የሰነድ ማስረጃ አስደግፎ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት አቅርቧል::

ተከሳሽ በችሎት ቀርቦ ማንነቱ ከተረጋግጠ በኃላ ክሱ ተነቦለት እንዲረዳዉ የተደረገ ሲሆን ተከላከል በተባለበት የክስ መዝገብ የወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዶ በመከራከሩ የዐቃቤ ሕግ ምስከሮች ቀርበው ተሰምተዋል፡፡ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹን በቀረበበት የክስ መዝገብ ጥፋተኛ ነህ ብሎታል::

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱም መዝገቡን መርምሮ የቅጣት ሀሳብ ተገቢ ከሆነዉ የህግ ድንጋጌና የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ጋር በማገናዘብ ተከሳሽ የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን ማቅለያ በመያዝ ተከሳሽን ያርማል ሌሎችን ያስተምራል በሚል በ20 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል::(ምንጭ ፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top