Connect with us

“ፌስቡክን ለመክሰስ እያሰብኩ ነው”- አትሌት ኃይሌ ገ/ሰላሴ

"ፌስቡክን ለመክሰስ እያሰብኩ ነው"- አትሌት ኃይሌ ገ/ሰላሴ
Photo: ARTICLE 19

ህግና ስርዓት

“ፌስቡክን ለመክሰስ እያሰብኩ ነው”- አትሌት ኃይሌ ገ/ሰላሴ

ዝነኛው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ፌስቡክን ለመክሰስ እያሰበ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታወቀ፡፡

አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች የከፋ ጉዳት እንዲያደርሱ የማህበራዊ የትስስር ገጾች በተለይም ፌስቡክ ትልቅ ድርሻ እንደነበረው ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ፌስቡክ እያደረሰ ላለው ጥፋት የማይከስ ከሆነ እኔ መክሰሴ አይቀርም ያለው ኃይሌ ሃገር እየተጎዳ ነው፤ ህዝብም እየሞተ ነው ብሏል፡፡

በጥቂት ቀናት ውስጥ የበርካቶች ህይወታቸውን ማጣታቸውን የገለፀ ሲሆን ይህም ፌስቡክን ለመጠየቅ በቂ ነው በማለት ተናግሯል፡፡

ፌስቡክን ለትግል እና ለነጻነት ድምጽ ማሰሚያ አውለነዋል የሚል ሃሳብ ቢነሳም፤ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ሊያስከፍል እንደማይገባና ጥነቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

ማንም ሰው ውሎ አድሮ ለሰራው ጥፋት ከተጠያቂነት አያመልጥም ሲል ነው የተናገረው፡፡

አትሌት ኃይሌ ከፌስቡክ ባሻገር ኢትዮጵያ ውስጥ የተከፈቱ ሚዲያዎች በጥንቃቄ መስራት እንዳለባቸው አሳስቧል።

በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ደጋፊዎቻቸው የሚያደርሷቸውን ምስሎች እና ጽሁፎች ላይ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም ተናግሯል፡፡

አትሌት ኃይሌ ሌላ አገር የተፈጠሩ እዚህ አገር እንደተፈጠሩ፣ ሌላ ሃገር የተቆረጡ እጆችና እግሮች እዚህ አገር እንደተቆረጡ፣ ሌላ አገር የተቃጠሉ ቤቶች እና ንብረቶች እዚህ አገር እንደተቃጠሉ አድርጎ ለጣጥፎ ማቅረብ፤ አድራጊውን ሰው ኋላ ላይ ዋጋ ያስከፍለዋል።’’ ብሏል፡

አሁን ቁጭ ብሎ ቢያይ ነገ ከተጠያቂነት አያመልጥም ሲል በዚህ ተግባር የተሰማሩ አካላት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top