Connect with us

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ ከተመድ ረዳት ዋና ጸሃፊ እና የሰላም ማስከበር ጉዳዮች ሃላፊ ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ ከተመድ ረዳት ዋና ጸሃፊ እና የሰላም ማስከበር ጉዳዮች ሃላፊ ጋር ተወያዩ

ማህበራዊ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ ከተመድ ረዳት ዋና ጸሃፊ እና የሰላም ማስከበር ጉዳዮች ሃላፊ ጋር ተወያዩ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ጸሃፊ እና የሰላም ማስከበር ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑትን ሚስተር ጂን ፒየር ላክሯ ትናንት ጥቅምት 19 ቀን 2012 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በነበራቸው ውይይት ኢትዮጵያና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ቀንድ ሰለም ማስከበር ሂደት በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች እንዲሁም በቀጠናው ስላለው የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮቸ ዙሪያ ትኩረት ሰጥተው መክረዋል።

ሚኒስትር አቶ ገዱ በኢትዮጵያ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መከካል ያለውን የቆየ ጠንካራ ግንኙነት በማስታውስ ተመድ በአፍሪካ እና በቀጠናው ሰላምን ለማስፈን እያደረገ ስላለው እንቅስቀሴ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ እንደ አገር እና በኢጋድ ሊቀመንበርነቷ በቀጠናው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፈን በአደራዳሪነት፣ ግጭትን አስቀድሞ በመከላከል እና በሰላም ማስከበር ተልዕኮ በመሳተፍ እያደረገች ያለውን እንቅስቅሴ በተመለከተ ክቡር ሚኒስትር አቶ ገዱ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሱዳን የተመሰረተው የሽግግር መንግስት በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም በማስፈን ልማትን ለማፋጠን እንዲችል ኢትዮጵያ ከሽግግር መንግስቱና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራች መሆኗን ክቡር ሚኒስትር ገልጸዋል።

በደቡብ ሱዳን ያለው የሰላም እንቅስቃሴ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑንና ሁሉም ወገኖች ለደቡብ ሱዳን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ሲሉ ተቀራርበው እንዲሰሩ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገች መሆኗንም ክቡር ሚኒስትር አቶ ገዱ አብራርተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። ሚስተር ላክሯ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቀጠናው ዘላቂ ሰላም አንዲሰፍን እያደረገች ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ጥላ ስር በሚካሄዱ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ስላላት ግንባር ቀደም ሚናም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ስለደረሰችው የሰላም ስምምነት እና በሱዳን ሰላም አንዲሰፍን ስለተጫወተችው ሚና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በኢጋድ በኩል በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እያደረገች ያለው እንቅስቃሴ በውጤት አንደሚጠናቀቅ እምነታቸው መሆኑንም ሚስተር ላክሯ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቀጠናው ለምታደረገው የሰላም እንቅስቃሴ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድጋፉን አጠናከሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ቃል አቀባይ ጽ/ቤት
ጥቅምት 19 ቀን 2012 ዓ.ም

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top