Connect with us

“ ወንጀል አልፈጸምኩም፤ ጥፋተኛም አይደለሁም” – አቶ አብዲ

“ ወንጀል አልፈጸምኩም፤ ጥፋተኛም አይደለሁም” – አቶ አብዲ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

“ ወንጀል አልፈጸምኩም፤ ጥፋተኛም አይደለሁም” – አቶ አብዲ

“ ወንጀል አልፈጸምኩም፤ ጥፋተኛም አይደለሁም” – አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዚደንት

የቀድሞው ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል “ክልሉን በጥሩ ሁኔታ ከማስተዳደር ውጪ ወንጀል አልፈጸምኩም፤ ጥፋተኛም አይደለሁም” አሉ፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት የአቶ አብዲ መሐመድ ኡመርን የእምነት ክህደት ቃል ዛሬ ተቀብሏል፡፡

በሌላ በኩል በአብዲ መሐመድ ኡመር የክስ መዝገብ እስካሁን ያልቀረቡ ሰባት ተከሳሾች የጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸውና ውጤቱ ለህዳር 22/2012 ዓ.ም እንዲቀርቡ ችሎቱ ትዕዛዝ መስጠቱን ዋልታ ኢንፎ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም በቁጥጥር ስር ካልዋሉ ተከሳሾች ጋር በተያያዘ የፍትህ መዛባት እየደረሰባቸው መሆኑን ከጠበቆችና ከተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ቀርቧል፡፡ ይህም ባለፉት 15 ወራት ያልተያዙ ተከሳሾች እንዲያዙ የሚደረገው ፍለጋ አሁንም ባለመቆሙ ምስክር የመስማትና የማስረጃ ማመሳከር ቀጣይ ሂደት እንዳይፈጸም እንቅፋት ስለመሆኑ ነው የገለጹት፡፡

ፍርድ ቤቱ የተፈጠረው መጓተት ባሉ የተንዛዙ አሰራሮች ጋር በተያያዘ በመሆኑ ወደፊት በተፋጠነ መልኩ ፍትህ የሚሰጥበትን ሁኔታ እንደሚያመቻች አስረድቷል፡፡

አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር በሶማሌ ክልል ሐምሌ 2010 ዓ.ም ዘርና ኃይማኖትን ለይቶ በተፈጸመው ጥቃት ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡ በወቅቱም ከደረሰው የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት በተጨማሪ 59 ሰዎች መገደላቸው በክሱ መብራራቱም የሚታወስ ነው፡፡(ምንጭ፡-ኢፕድ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top