Connect with us

ማቀፍን ምን አመጣው? መታቀፍስ ስለምን የሌላው ዕጣ ሆነ?

ማቀፍን ምን አመጣው? መታቀፍስ ስለምን የሌላው ዕጣ ሆነ?
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ማቀፍን ምን አመጣው? መታቀፍስ ስለምን የሌላው ዕጣ ሆነ?

ማቀፍን ምን አመጣው? መታቀፍስ ስለምን የሌላው ዕጣ ሆነ? አቃፊና ታቃፊው ድራማ ቀርቶ እንደ ጥንቱ መተቃቀፋችን ለምን ተጠላ?
****
ከስናፍቅሽ አዲስ
ማቀፍ መታቀፍ የጥፋት ማግስት ፕሮፖጋንዳ ከሆነች ቆየች፡፡ እኔም ያልገባኝ ይሄው ነው፡፡ ማቀፍን ምን አመጣው? አቃፊነት ማለት እኮ እኔ ሰብሳቢ ነኝ ባይነት የጠቅላይ መሆን መሻት ነው፡፡ የብሔር አቃፊና የብሔር ታቃፊ ከብዝሃነት ፍልስፍና ጋር በእጅጉ የሚቃረን የአውራነትና የተከታይነት እሳቤ ነው፡፡

ፍቅርን ለመስበክ የቀደሙት በየቤታቸው የሆኑት በቂ ነው፡፡ ዛሬም ያቀፈ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ የደቡብ ሰው፣ የምስራቅ ሰው በየቤቱ ባል ሆኖ አለ፡፡ ዛሬም የታቀፈች የምዕራብ ሰው የሰሜን ሰው ደቡብ ሰው የምስራቅ ሰው ሚስት ሆና በየቤቱ አለች፡፡ በትዳር ማቀፍ መተቀፍ እርግጥ ነው ውህድ ህዝብ ይፈጥራል፡፡

ብሔር አቃፊ ነው ማለት ከፌዴራሊዝሙ ጽንሰ ሀሳብ የራቀ የግነት ወሬ ነው፡፡ የቱ ብሔር የቱን ያቅፋል፤ በምን አግባብስ አቃፊ መሆኑን ትነግረኛለህ? የታቀፈው ቢሆንስ ያቀፈው፤ በቁጥር መብዛትን እንደ የማቀፍ መብት አጎናጽፎ ሌላውን ታቃፊ ማለት፣ መጤና ነባር የምትለዋን እኩይ ቃል በዘዴ መግለጽ ይመስለኛል፡፡

እንደ ህዝብ የሚያስፈልገው የብሔሮቻችን መተቃቀፍ ነው፡፡ መተቃቀፍ የአንድ ወገን ሀሳብ አይደለም፡፡ የተጠለፈች ሚስቱን አቅፎ የሚሄድ ባል ማየት ይቻላል፡፡ ለመተቃቀፍ ግን የእሷም በእሱ መታቀፍን መፈለግ የግድ ይላል፡፡ የሚበጀን መተቃቀፍ እንጂ በየጥቂት ቀኑ በጭካኔ ሰርፕራይ እያደረጉ ማቀፍ አይደለም፡፡

የኦሮሞ አባቶችም ሆኑ የገዳ መሪዎች አብሮ መሆንን እንጂ እኛ የሌላው አቃፊ ነን ማለትን የኖሩበት ባህል የለመዱት ቋንቋ አይደለም፡፡ እንደ ጉዲፈቻና ሞጋሳ ያሉ ባህሎችም ቢሆኑ ከማቀፍ ከፍ ያለ ሀሳብ ያላቸው ረቂቅ ፍልስፍናዎች ናቸው፡፡ ራስን ማድረግ ማቀፍ ሳይሆን ማዋሃድ ነው፡፡

እናም አቃፊ ነው ይሏት ቃንቋ የሚታቀፍ መኖሩን እንጂ መተቃቀፍን አትሰብክም፡፡ የሚታቀፍ ደግሞ የማቀፍ መብት ሳይሆን ሁሌም የመታቀፍ ግዴታ ያለበት መሆኑን የምትጠቁም ውስጠ ዘ ናት፡፡ ቅኔዋን ስንፈታት የኬኛ ጽንሰ ሀሳብ ማር ተቀብታ መምጣቷን እንረዳለን፡፡ ብንቀምሳት ግን እሬት ናት፡፡ እናም እንተቃቀፍ እንጂ እንታቀፍ ያለ የለም ማለት ፈለግሁ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top