Connect with us

ድሮም ሀገሬን ላፍርስሽ የሚላት ጠፍቶ ሳይሆን የሚሰራት በርትቶ ነው እዚህ የደረሰችው

ድሮም ሀገሬን ላፍርስሽ የሚላት ጠፍቶ ሳይሆን የሚሰራት በርትቶ ነው እዚህ የደረሰችው
Photo: ያሬድ ሹመቴ

ባህልና ታሪክ

ድሮም ሀገሬን ላፍርስሽ የሚላት ጠፍቶ ሳይሆን የሚሰራት በርትቶ ነው እዚህ የደረሰችው

ድሮም ሀገሬን ላፍርስሽ የሚላት ጠፍቶ ሳይሆን የሚሰራት በርትቶ ነው እዚህ የደረሰችው፡፡ በወገን እርዳታ ርብርቡ ኮራሁ፤  | ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ሀገሬ እዚህ የደረሰችው የውጪ ወራሪን መክታ ብቻ አይደለም፡፡ ጡቷን ጠብቶ አንገቷን መቅላት የሚፈልግ የራሷ ልጅም አይንሽም አልይሽ ሲላት ኖራ ነው፡፡ ኢትዮጵያን የሚጠላ ኢትዮጵያዊ ማየት ትናንትም ዛሬም ብቅር አይደለም፤ ነገም እንዲህ ያለው ይፈጠራል፡፡ ሀገር የኖረችው ግን አብልጦ የሚወዳት ራሱን እየሰጠላት ነው፡፡

ከወራሪ ጋር አብረው፣ በሆዳቸው ጉዳይ አኩርፈው፣ ከነገስታት ቂም ይዘው ከሚያፈርሳት ጋር ሊያፈርሷት የሞከሩት ብዙ ናቸው፡፡ የሚሰሯት ጉልበት ግን ብርቱ ነበር፡፡ የሚወዷት ፍቅር ግን ጽኑ ነበር፡፡ እናም ይህ ከዚያኛው በልጦ ዛሬ ደርሳለች፡፡

ሰሞኑን በበጎ ፍቃደኞች ዳግም ያየነው ይሄንን ነው፡፡ ጎራ መለየት ግድ በሆነበት ሰዓት ጎራ ለማይለየው ችግር አለን ብለው ጥሪ አሰሙ፡፡ ወገን በየስፍራው ወድቋል፡፡ ቤት ጥሎ መሄድ መማለጥ ከተቻለ ስኬት ነው፡፡ እንዲህ ሆኖ የወጣው ሜዳ ላይ ሲወድቅ ሀገር ማለት ሰው ነው ብለው ኑ እንደጋገፍ አሉ፡፡

ጥሪው ጆሮ አግኝቷል፡፡ የምናየውና የምንሰማው መተባበር የበጎ ፍቃደኞቹን ልብ ብቻ ሳይሆን የሀገርን ምሰሶ የሚያጠበቅ መልካም ቱሩፋት ነው፡፡ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ ወደ ተጣለው ተመልክተዋል፤ ለተቸገረው እንድረስ ብለዋል፡፡

እንዲህ ያለውን ጥሪ ከመስማት በላይ ምን መልካም ነገር አለ፤ የመዲናዋ ሰው የቻለውን ለማድረግ አልሳሳም፡፡ እንዲህ ያለው መልካም እሴት በኔ ዘመን ወጣቶች ሲሆን መመልከት ተስፋ ነው፡፡ በኔ ዘመን ብዙ ክፉ ነገሮች አሉ፤ እዚያ ክፋት አናት ቆሞ ደግ ማድረግ ግን ከአድዋ የማይተናነስ ተጋድሎና ጀግንነት ነው፡፡

ሰሞኑን ሰው ለማስጣል ስላለቀሱ አንድ የኦሮሞ አባት የሰማሁት ልቤን ሞልቶት ነበር፡፡ እንዲህ መሆን የአባቶች ብቻ ሳይሆን የዚህ ትውልድም ስጦታ መሆኑን ከአዲስ አበባ ወጣቶች አየሁ፡፡ ይህንን ጥሪ ማድመጥ ከምንም በላይ የሚያስደስታችሁ አሁንም ወጣቶቹ ኑ ለበጎነት አብረን እንቁም እያሉ ነው፡፡ አብረን በጎ ከሆንን ከተሳሰብን ድሉ የመልካሞች ይሆናል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top