Connect with us

በመስከረም ወር ከዕቅዱ ያነሰ የወጪ ንግድ ገቢ ተገኘ

በመስከረም ወር ከዕቅዱ ያነሰ የወጪ ንግድ ገቢ ተገኘ

ኢኮኖሚ

በመስከረም ወር ከዕቅዱ ያነሰ የወጪ ንግድ ገቢ ተገኘ

በ2012 በጀት ዓመት በመስከረም ወር ከግብርና፣ ከማኑፋክቸሪንግ እና ከማዕድን ምርቶች ዘርፍ 255 ነጥብ 64 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ የተከናወነው 202 ነጥብ 81 (79 ነጥብ 33%) ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ነው፡፡

ይህ አፈፃፀም ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ከተገኘው 177 ነጥብ 76 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ጋር ሲነጻጸር 25 ነጥብ 05 (14 ነጥብ 09%) ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በመስከረም ወር ከተያዘላቸው ዕቅድ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡ የወጪ ምርቶች የብዕርና አገዳ እህሎች፣ የተፈጥሮ ሙጫና ዕጣን፣ አበባ፣ ሻይ ቅጠል እና ኤሌክትሪክ ናቸው፡፡ የዕቅዱን ከ75% እስከ 99% ክንውን ያስመዘገቡ ምርቶች የጥራጥሬ ሰብሎች፣ ጫት፣ ቡና እና ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ናቸው፡፡

ከተያዘላቸው ዕቅድ 50% እስከ 74% ክንውን ያሰመዘገቡ ምርቶች ባህር ዛፍ፣ የቅባት እህሎች፣ ወተትና የወተት ተዋፅኦ፣ ሰም፣ የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት፣ የቁም እንስሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እና አትክልትና ፍራፍሬ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ለወሩ ከተያዘው ዕቅድ አንጻር በውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ50 በመቶ በታች ዝቅተኛ ክንውን ያስመዘገቡ የወጪ ንግድ ምርቶች እንደቅደም ተከተላቸው ምግብ መጠጥና ፋርማስዩቲካልስ፣ ታንታለም፣ ቅመማ ቅመም፣ ሌሎች ማዕድናት፣ የሥጋ ተረፈ ምርት፣ ወርቅ፣ ማር እና ኤሌክትሮኒክስ ናቸው፡፡

በቀጣይ የወጪ ምርቶችን በጥራት፣ በተወዳዳሪ ዋጋና በሚፈለገው መጠን ለዓለም ገበያ ለማቅረብ የአሰራር ሥርዓትን መዘርጋት፤ የምርት ግብይቱን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ ግልፅ እና ፍትሀዊ ማድረግ፣ ገበያ ተኮር ምርቶችን በዘመናዊ ግብይት ሥርዓቱ ውስጥ ማስገባት እና ሌሎች ተገቢ የሆኑ እርምጃዎችን በአፋጣኝ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ በአጠቃላይ ለዘርፉ ዕድገትና ስኬት እውን መሆን የሁሉንም ባለድርሻ አካላትን ርብርብ ይጠይቃል፡፡

(ምንጭ የንግድና ኢንደስትሪ ሚ/ር)

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top