Connect with us

የሁለት ዘመናት ዜማዎች

የሁለት ዘመናት ዜማዎች
YouTube

ባህልና ታሪክ

የሁለት ዘመናት ዜማዎች

ከሰሞኑ በተለያዩ የማህበራዊ ድህረገፆች አንድ ዘፈን አይሉት ፉከራ ነገር ተለቆ ብዙ ሰዎች ሲቀባበሉት እና ሲያጋሩት ተመለከትኩ፡፡ እናም ምን ይሆን ብዬ ምስሉን ፈልጌ ተመለከትኩት(ኋላ ላይ በማየቴ ብፀፀትም) ሙዚቃው ተጀመረ

…ሲጀምር፤ ኢትዮጲያ ጥያቄ አለኝ ብሎ ጀመረ ድምፃዊው(ድምፃዊ ለማለት አስቸጋሪ ነው) ቀጠለ;- አዲስ አባ አዲስ አባ የሚቲሉት ለሚንዲኖ መሊሱሊኝ ያኒቴ ኢጅ ቲቆርጣሌ—-አልቆርጢም ያኒቴ ኢጊር ቲቆርጣሌ—-አልቆርጢም ያኒቴ ኢንቢርት ቲቆርጣሌ—-አልቆርጢም ሲለዚ አዲሳባ የኦሮሞ ኢንቢርት ሲለሆነ አቲቆረጢም አይሰጢም ገባህ—— እያለ ይቀጥላል

በተኮላተፈ አማርኛው ሲማ የኔ ቤት ኢኮ ነው እያለ ዘፈኑ ይቀጥላል፡፡ ይህ ዘፈን በምስል የታገዘ ስለሆነ ምስሉ ላይ ዘፋኙ ከጓደኞቹ ጋር ሆኖ ከአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ አንድን ቤተሰብ እየደበደቡ ሲያስወጡ ይታያል ፡፡

እንግዲህ እንደዚህ አይነት አሳዛኝ የዘረኝነት ምዕራፋችን የት እንደደረሰ የሚያሳይ ዘፈን ግጥም ተፅፎለት፤ ዜማ ተሰርቶለት፤ በሙዚቃ መሳሪያ ተቀናብሮ፤ በምስል ተቀርፆ የምናይበት እና የምንሰማበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ ይህንን ዘፈን መመልከት በእውነት እንደ አንድ ኢትዮጲያዊ የሚያሳፍር ነው፡፡ ዘፈኑ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ወይም የአዲስ አበባ ጉዳይ አይደለም፤ ይልቁንስ ተራ የዘረኝነት ማሳያ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

እጅግ አሳዛኙ ነገር ደግሞ በዘፈኑ ላይ ህፃናት ጭምር ተሳትፈውበታል ይህንን ስመለከት በሀገሬ ላይ ተስፋ ላለመቁረጥ ስታገል የኖርኩትን ያህል ፍርሀት ተሰማኝ፡፡ ይህቺ ምስኪን ሀገር ቀጣይ እጣፈንታዋ ሀገር በዘር ተከፋፍላ የምንለው ሁሉ በዘር በብሄር እየተመነዘረ እንዴት እንኖራለን የሚለው ያስጨንቃል፡፡

ኢትዮጲያዊነት ተዘንግቶ ብሄር እና ዘር ጎልቶ የማንነት መለኪያ በሆነበት በዚህ ሰኣት ስለነገው ስለልጆቻችን አብሮነት ማሰብ ከባድ እየሆነ መጥቷል ፡፡ ያኔ በደጉ ዘመን :-

የማንነቴ መለኪያ ኩራቴ መመኪያዬ ክብሬ፤
የሶስት ሺህ አመት እመቤት
አንድ ናት ኢትዮጲያ ሀገሬ ፡፡——- ነበር ሙዚቃችን፤ እንዲህ እያልን ነበር የሀገር ፍቅር ስሜታችንን በምርጥ ጥዑመ ዜማዎች የምናጣጥመው ፡፡

ዛሬ ግን ሁሉም ነገር የተገላቢጦሽ ነው፡፡ እነ ጥላሁን ገሰሰን፤ እነ ጂጂን፤ እነ አሊ ቢራን ስለሀገር ስለ አንድነት ሲዘፍኑ በሰማንበት ጆሮ ዛሬ ይህንን መስማት ምነኛ ይጎረብጣል? ጥበብ ስለፍቅር ስለአንድነት ስትሰብክ እንጂ ስለጥላቻና መከፋፈል ስትሰብክ መስማት እንዴት ይከብዳል?

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top