Connect with us

የቀድሞ የዕንቁ መጽሔት ባለቤት በሰባት ዓመት እስራት ተቀጣ

የቀድሞ የዕንቁ መጽሔት ባለቤት ፍቃዱ ማኅተመወርቅ በሰባት ዓመት እስራት ተቀጣ

ህግና ስርዓት

የቀድሞ የዕንቁ መጽሔት ባለቤት በሰባት ዓመት እስራት ተቀጣ

ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ከአምስት ዓመታ በፊት በዕንቁ መጽሔት በተመሰረት ክስ ማክሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2012ዓ.ም በዋለው ችሎት ጥፋተኛ በመባሉ በሰባት ዓመት እስራት እና የሰባት ሽሕ ብር የገንዘብ መቀጮ ተፈርዶበታል።

ፍርድ ቤቱ ግለሰቡን ከታክስ ስወራ ጋር በተያያዘ ክስ መስርቶበት የነበረ ሲሆን ከዚህም ጋር በተያያዘ ከ2004 እስከ 2006 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ 179ሽሕ 411 ብር ከ65 ሳንቲም ለመንግስት መክፈል የነበረበትን ግብር ስወራ አድርጓል የሚል ክስ ተመስርቶበት ነበር።

(ምንጭ፡-አዲስ ማለዳ)

===

January 2015

የዕንቁ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው አቶ ፍቃዱ ማህተመወርቅ፤ የሃገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ‹‹ተገቢውን ግብር ለመንግሥት ገቢ አላደረክም›› በሚል ክስ ከጥር 13 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንዲውል አድርጎታል።

አቶ ፈቃዱ ከኢትዮጵያ ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የቀድሞ ጉምሩክ መ/ቤት ወይም በአሁኑ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የፀጥታና የሕግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት ቅጽር ግቢ በሚገኘው እስር ቤት የሚገኝ ሲሆን ፖሊስ ሐሙስ ጥር 14 2007 ዓ.ም ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ከሠላሳ አራዳ ጊዮርጊስ ፍ/ቤት ያቀረበው ቢሆንም የዋስትና መብቱ ሳይጠበቅ ለጥር 21 ቀን ከቀትር በኋላ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶት ወደ እስር ቤት ተመልሷል።

አቶ ፍቃዱን ያሳሰረው የሃገር ውስጥ ገቢ ማሰባሰቢያ መ/ቤት ‹‹የዕንቁ መጽሔት እየታተመች በነበረችበት ጊዜ የመጽሔቷ አሳታሚና ባለቤት ለመንግሥት ገቢ ማድረግ የሚገባቸውን 600 ሺኅ ብር አስቀርተዋል›› የሚል ሲሆን ፍ/ቤት ቀርቦም ‹‹ግለሰቡን በሕግ የምጠይቅበትን ሠነድ አሰባስቤ ያልጨረስኩ በመሆኑ ለሰባት ቀናት በእስር ላይ ይቆዩልኝ…›› የሚል ጥያቄ አቅርቦ ለጊዜው በፍርድ ቤቱ በኩል ተቀባይነት አግኝቷል።

የዕንቁ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው አቶ ፈቃዱ ማህተመ ወርቅ ‹‹ፖሊስ የመሰረተብኝ ክስ እኔን የሚመለከት አይደለም ›› ያሉ ሲሆን፤ በሕግ የሚጠየቁበት ጉዳይ ካለም የዋስትና መብታቸውን ሊያስነፍግ እንደማይችል፣ ሕጉም በአግባቡ የሚተረጎም ከሆነ ከእስር ነጻ የመሆን ዕድል እንዳላቸው ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top