Connect with us

በሰሞኑ ጥቃት ከ3 ሺ 366 በላይ ወገኖች ተፈናቅለዋል

በሰሞኑ ጥቃት ከ3 ሺ 366 በላይ ወገኖች ተፈናቅለዋል
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በሰሞኑ ጥቃት ከ3 ሺ 366 በላይ ወገኖች ተፈናቅለዋል

ሰሞኑን በተለያዩ አካባቢዎች በተነሱ ግጭቶች ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ባሉበት ቦታ እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ።

የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ዳይረክተር አቶ ደበበ ዘውዴ እንደገለጹት፥ ባለፈው ሳምንት ተከስቶ በነበረው ግጭት ከምእራብ አርሲ ዶዶላ ተፈናቅለው በሁለት ቤተክርስቲያናት ለሚገኙ ዜጎች የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎች ተልኳል።

በዶዶላ 3 ሺህ 366 ዜጎች የተፈናቀሉ ሲሆን፥ እህል፣ የአልሚ ምግብ፣ ዘይት፣ ጥራጥሬ፣ ብስኩትና ሌሎች ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎች እንዲደርሳቸው ተደርጓልም ነው ያሉት።

በሰበታም በተመሳሳይ 1 ሺህ 100 ዜጎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን፥ ለእነሱም ባሉበት ቦታ የአንድ ወር እርዳታ እንዲያገኙ መደረጉን ጠቅሰዋል።

ለተጎጂዎቹ ከምግብ እህል ውጭም ብርድ ልብስ፣ ፍራሽ፣ ሳሕንና ብርጭቆን ጨምሮ የማብሰያ እቃዎች መላካቸውንም አስረድተዋል።

ኮሚሽኑ አደጋ ሲከሰት በ72 ሰዓት ውስጥ ድጋፍ የማቅረብ ግዴታ ያለበት በመሆኑ እራሱን ዝግጁ አድርጎ እንደሚቀመጥም አስረድተዋል።

(ምንጭ፦ ኢዜአ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top