Connect with us

መንግስት ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ፤ እየደረሰ ያለው ጉዳት እየባሰ መጥቷል

መንግስት ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ፤ እየደረሰ ያለው ጉዳት እየባሰ መጥቷል
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

መንግስት ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ፤ እየደረሰ ያለው ጉዳት እየባሰ መጥቷል

“መንግስት ኃላፊነቱን ባለመወጣቱ፤ እየደረሰ ያለው ጉዳት እየባሰ መጥቷል”
-“ወንጀለኞቹ ከሰው ፍርድ ቢያመልጡ-ከእግዚአብሐር ፍርድ አያመልጡም”

– የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል የተከሰተው ጉዳት እንዳሳዘነው የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት አስታወቀ
ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል የተከሰተው ጉዳት እንዳሳዘነው የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ ክቡር የሰው ልጅ በግለሰቦችና በመንግስት ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱ አሳዛኝ መሆኑን የቤተክርስቲያናቱ መሪዎች ገልጸዋል፡፡

በዚህም ሰውን በዘርና በሃይማኖት ማጥቃት በምንም መስፈርት ተቀባይነት እንደሌለውና በእግዚአብሔር ፊትም የሚያስጠይቅ ነው ብለዋል፡፡

ከሁኔታው ጀርባ በቀጥታም ሆነ በስውር ያሉ ሰዎች ከህግ ቢሰወሩም እንኳን በእግዚአብሔር ፍርድ ሊያመልጡ እንደማይችሉም ነው የተገለፀው፡፡

የመብት ረገጣና ጭቆናን እንቃወማለን የሚሉ ሰዎች ይሄንን ተላልፈው ለሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት ውድመት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ የጥላቻ ንግግሮች ህዝብን እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚያደርጉትን ተግባር እንደሚያወግዙም ነው የአብያተ ክርስቲያናቱ መሪዎች የተናገሩት፡፡

መንግስት እንደ መንግስት የሁሉንም ዜጋ መብት ማስጠበቅ በሀገራችን ሰላምን ማረጋገጥ እና ህገ የበላይነትን የማስከበር ሓላፊነቱን ባለመወጣቱ እየደረሰ ያለው ጉዳት እየተበራከተ መጥቷል፤ በዚህም መንግስት የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ ለነገ የማይባል በመሆኑ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በጋራ ጥቅምት 21 እና 28/2012 ዓ.ም በምስራቅ አጥቢያ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የንስሃና የምልጃ ፀሎት እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

እንዲሁም ወንጌላዊያንና አማኖች ከጥቅምት 24 እስከ 27/2012 ዓ.ም በያሉበት ፀሎት እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን የአስተላልፈዋል፡፡

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top