Connect with us

የጀዋር መሐመድ ጥሪ

የጀዋር መሐመድ ጥሪ "የተጣላችሁ ታረቁ፣ ጉዳተኞችን እርዱ!"

ህግና ስርዓት

የጀዋር መሐመድ ጥሪ

የጀዋር መሐመድ ጥሪ “የተጣላችሁ ታረቁ፣ ጉዳተኞችን እርዱ!” | ታምሩ ገዳ

ለአክቲቪስት ጀዋር መሐመድ ከመንግስት የሚደረግለት የደህንነት ጥበቃ ሊቋረጥ ነው የሚል ወሬን ተከትሎ መዲናይቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ለተቃውሞ እና ለአመጻ ለወጡ ደጋፊዎቹ ጀዋር ጥሪ አቀረበላቸው።

ዜና አገልግሎት ሮይተርስ የጀዋር መኖሪያ ቤት ከሚገኝበት በአዲስ አበባ ከተማ ጃፖን ኢምባሲ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ተገኝቶ እንደዘገበው ከተፈጠረው ውጥረት እና ውዥንብር ጋር በተያያዘ ለጀዋር ድጋፋቸውን እና ጥበቃ ለማድረግ በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ ለከተሙት ብዛት ያላቸው ወጣቶች ባስተላለፈው መልእክቱ” የተዘጉ መንገዶችን ክፈቱ፣ በግጭቱ ሳቢያ የቆሸሹ ጎዳናዎችን አጽዱ፣በአመጻው የተጎዱ ወገኖችም አስታምሙ፣ ከተጣላችኋቸው ጋርም እርቀ ሰላም ፍጠሩ”ብሏል።

ምንም እንኳን አክቲቪስት ጀዋር በወቅቱ መንግስት ፣ተስፋ ቆርጠናል የሚሉ ፣ ደጋፊዎቹ ሆኑ በስሜት ተገፋፍተው ወደ አደባባይ የወጡ ወጣቶችን አደብ እንዲገዙ መመሪያ ቢሰጥም እርሱ እራሱ ለአገሪቱ እና ለህዝቦቿ ዘላቂ ሰላም እና ደህንነት ሲባል ምን አይነት መልካም የሆነ እና በተግባር የሚታይ አርያነትን ሊከተል እንዳሰበ በውል አልገለጸም። ወጣቶቹም ቢሆን ከዚህ በሁዋላ ተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ በመግባት የራሳቸውንም ሆነ የማህበረሰቡን ደህንነት አደጋ ላይ ላለመጣላቸው ምንም አይነት ማረጋገጫ የለም።

እሮብ እለት በተቀሰቀሰው ያለመረጋጋት በትንሹ ከሀያ ሰባት በላይ ዜጎች ህይወታቸው የተቀጠፈ ሲሆን ብዛት ያላቸውም ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታሎች ተወስደዋል።በአንዳንድ አካባቢዎችም ነጋዴዎች ዘራቸው እና ሀይማኖታቸው እየተመረጠ ንብረቶቻቸው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል እንደ ወደሙባቸው አለማቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ። ስለጠፋው የሰው ህይወት እና የንብረት ውድመት እስከአሁን ድረስ በይፋ ሀላፊነቱን የወሰደ መንግስታዊ አካል ወይም ግለሰብ የለም።

በጀዋር መኖሪያ ቤት አካባቢ ከተሰባሰቡ ብዛት ያላቸው ወጣቶች መካከል እንዳንዶቹ ድንኳን በመትከል ” ዶ/ር አብይ አህመድን አንፈልግም “የሚል መፈክር ሀሙስ እለት ሲያሰሙ እንደነበር እና እንዳንዶቹም ከመንግስት በቂ መረጃ እስከሚያገኙ ድረስ ወደ ቤታቸው ከመመለስ ለቀጣዩ ቀናት እና ሳምንታት ከአካባቢው ለመቆየት መወጠናቸውን ለሮይተርስ ገልጸዋል።

በአንድ ወቅት የዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደርን በቀንደኝነት በመደገፍ የሚታወቀው ጀዋር መሐመድ የሚሰጣቸው ብሔር ተኮር አስተያየተቶቹ ቅሬታ ያሳደረባቸው ቀላል የማይባሉ ወገኖች የመኖራቸውን ያህል በተቃራኒው በበርካታ የኦሮሞ ወጣቶች ዘንድ እንደ “ጀግና ” ተደርጎ መወሰዱን የጠቆመው የሮይተርስ ዘገባ ኢትዮጵያ ከወራት በሁዋላ ታካሄደዋለች ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ ላይ ጀዋር ገዢው ፖርቲን በመደገፍ አሊያም በተቃራኒ ጎራ ሊሰለፍ ይችላል ሲል ገምቷል።

ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ የአለም የሰላም ኖቤል ሽልማት ባገኙ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በትውልድ ክልላቸው እና በርካታ ድጋፍ እንዳላቸው በሚገመተው በኦሮሚያ የክልል ከተሞች ውስጥ ይህ አይነቱ አሳዛኝ እና ሊደረግ የማይታለም ግጭት እና እልቂት መከሰቱ በብዙዎች ዘንድ ብርቱ ፈተናዎች ከፊት መደቀናቸውን እና አስተዳደሩም ቢሆን በአለታማ መደላድል ላይ አለመቆሙን ያመላክታል ሲሉ የፖለቲካ ተንታኞች ስጋታቸውን ይገልጻሉ።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top