Connect with us

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ የመንግሥት ልኡክ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋራ ይነጋገራ

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ የመንግሥት ልኡክ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋራ ይነጋገራ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ የመንግሥት ልኡክ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋራ ይነጋገራ

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ የመንግሥት ልኡክ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋራ ይነጋገራል፤ ምልአተ ጉባኤው በሚቀርቡ ማስረጃዎች ላይ መምከሩን ቀጥሏል

በተወሰኑ የኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከት ከተሞች፣ በኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና አብያተ ክርስቲያን ላይ እየተፈጸመ ያለው የብሔር እና የሃይማኖት አክራሪዎች ጥቃት እና ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆም በማድረግ ጉዳይ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ የፌዴራል መንግሥት ልኡክ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤን እንደሚያነጋግር ተጠቆመ፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩን አቶ ለማ መገርሳንና የሰላም ሚኒስትሯን ወ/ሮ ሙፈሪአት ካሚልን ያካተተው ይኸው ልኡክ፣ ዛሬ ዓርብ፣ ጥቅምት 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ላይ ምልአተ ጉባኤውን ያነጋግራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምልአተ ጉባኤው ትላንት ጠዋት የሦስት ቀናት የጸሎት እና የምሕላ ዐዋጅ ካወጣና የሰላም ጥሪውን ካስተላለፈ በኋላ የቀጠለውን መደበኛ ስብሰባውን በድንገት በማቋረጥ፣ ከየአህጉረ ስብከቱ መድረስ የጀመሩ የጉዳት እና የስጋት መረጃዎችንና ሪፖርቶችን እያሰባሰበ መወሰድ ባለበት አቋም ላይ ሲወያይ አምሽቷል፤ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ደብዳቤ ለመጻፍ እና መግለጫም ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንደ ኾነ መገለጹ ይታወሳል፡፡

“በአሁኑ ሰዓት መሥመር እየለቀቀ የመጣውን፣ በምእመናንና በቤተ ክርስቲያን እየደረሰ ያለውን የማያባራ ጥፋት በጥብቅ ማቆምን ይመለከታል” በሚል ርእስ የተዘጋጀው መግለጫ እና ደብዳቤ ይዘት በዋናነት፣ የክልል የጸጥታ ኀይሎች በአካባቢው እያሉ ለርዳታ ቢጠየቁም ሊታደጉን አልቻሉም፤ ስለዚህ የፌዴራል መንግሥት ኀይሉን በውል አንቀሳቅሶ አፋጣኝ ርምጃ በመውሰድ ጥቃቱን ያስቁምልን፤ የሚል እና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤን በአስቸኳይ እንድታነጋግሩን በማለት የሚጠይቅ ነው፡፡

ለእነኚህ ጥያቄዎች አጽንዖት ተሰጥቶ ተገቢ እና አፋጣኝ ምላሽ የማይኖር ከኾነ፤ ለሚደርሰው የሕይወት እና የንብረት ጉዳት መንግሥት ሓላፊነቱን እንደሚወስድ፤ የምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ላይ የሚገኘው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ምእመናንን በማስተባበር እና ችግሮች ወደተፈጠሩባቸው ቦታዎች በመሔድ የግፍ ጽዋ ከሚቀበሉ አማኞች ጋራ በኀባር ሰማዕትነት ለመቀበል እንደሚገደዱ የሚያስጠነቅቅ ነው፡፡(ምንጭ :-ሐራ ተዋህዶ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top