Connect with us

ኢትዮጵያና ሩሲያ የኒውክለር ሀይልን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያና ሩሲያ የኒውክለር ሀይልን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል ስምምነት ተፈራረሙ
Photo: Facebook

ማህበራዊ

ኢትዮጵያና ሩሲያ የኒውክለር ሀይልን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኒውክለር ሀይልን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ ስምምነት በሩሲያ ሶቺ ተፈራረሙ፡፡

የሁለትዮሽ ስምምነቱ በሩሲያ ሶቺ እየተካሄደው ካለው የአፍሪካ ሩሲያ የኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን ነው የተፈረመው፡፡

እንደ ኤፍ ቢሲ ዘገባ የስምምነቱን ፊርማ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በዛሬው ዕለት አስቀምጠዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በፎረሙ ላይ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ይካሄዳል፡፡

ኢትዮጵያ በቅርቡ የኒውክለር ቴክኖሎጂን ለሃይል ምንጭነት መጠቀም የሚያስችላትን ተጨማሪ ፕሮቶኮል ፊርማ መፈረሟ የሚታወስ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ኒውክለርን ለማናቸውም ሰላማዊ ጥቅም በተለይም ለጤና፣ ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪ እና የኤሌክትሪክ ሀይልን ለማመንጨት ጭምር እቅድ አላት፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top