Connect with us

“ለውጡ ሐዲዱን ስቷል” – አርቲስት ታማኝ በየነ

“ለውጡ ሐዲዱን ስቷል” - አርቲስት ታማኝ በየነ
Facebook

ፓለቲካ

“ለውጡ ሐዲዱን ስቷል” – አርቲስት ታማኝ በየነ

“ለውጡ ሐዲዱን ስቷል” | አርቲስት ታማኝ በየነ

በዶ/ር ዐብይ አሕመድ አስተዳደር ብሔር ተኮር የፓለቲካ ኃይሎች ጫፍ መውጣታቸው አስመልክቼ እንዲታረም እንደአንድ ዜጋ ያደረኩት ጥረት አልተሳካም፤ ለውጡ ሐዲዱ ስቷል ብዬ አምናለሁ ሲል አርቲስት ታማኝ በየነ ለቢቢሲ አማርኛ በሰጠው ቃለመጠይቅ አስታወቀ።

አርቲስት ታማኝ እንዲህ ብሏል።”እንግዲህ ለውጥ መጥቷል ብሎ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ እ . . . የዛሬ ዓመቱን ሙቀት መለኪያ ባይኖረንም በእርቅና መቻቻል፤ ያለፈውን በመተው ወደፊት ለመራመድ፤ አብሮ ለመጓዝ የሚሉት ሃሳቦች ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተቀብሎት ነበር ማለት እችላለሁ። ሁሉም የሚለው ባያስማማን እንኳን 90 በመቶ ብንል ለእውነት የቀረብን ይመስለኛል።

ዶክተር ዐብይ ለዘመናት የሄድንበትን የመበቃቀል ስህተት ‘በአዲስ መንፈስ በይቅርታ እንሻገር’ ሲል እንደማንኛውም ዜጋ እኔም ደስ ብሎኝ ይሄን ሃሳብ ተቀብያለሁ። ይሄ እንግዲህ የሚሆነው ‘ኢትዮጵያ የሄደችበትን የመከራ ዘመን በማሰብ አንድ ቦታ ላይ እንዘጋዋለን’ የሚል እንደ አንድ ዜጋ እምነት ስለነበረኝ ነው።

አሁን ያሉትን ሁኔታዎች ስንመለከት በብሔር ተኮር ፖለቲካ ያሉ ኃይሎች ጫፍ እየወጡ ኢትዮጵያዊ የሚለውን የዜግነት ሃሳብ እየገፉ፤ ዜጎች እንደልባቸው እንደ ዜጋ የሚኖሩበትን እያፈረሱ የመገፋፋትና የማፈናቀል. . . እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ተፈጥሯል።

ይህ ሊታረም የሚችልበትን መንገድ እንደ አንድ ዜጋ በግሌ ሞክሬያለሁ ሊሰሙኝ የሚችሉ ባለሥልጣናትን ምን እያደረጋችሁ ነው? ብዬ ጮኼያለሁ፤ አዝናለሁ ይህን ስናገር ግን ተስፋ ሰጪ አይደለም። ያሰብነው ጋር እየሄድን አይደለም። ለውጡ ሐዲዱን ስቷል ብዬ ነው የማምነው” ብሏል።

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top