Connect with us

ጠ/ር ዐብይ አህመድ በመደመር መጽሀፍ ምረቃ ላይ ከተናገሯቸው የተወሰዱ ነጥቦች

ጠ/ር ዐብይ አህመድ በመደመር መጽሀፍ ምረቃ ላይ ከተናገሯቸው የተወሰዱ ነጥቦች
Office of the Prime Minister-Ethiopia

ፓለቲካ

ጠ/ር ዐብይ አህመድ በመደመር መጽሀፍ ምረቃ ላይ ከተናገሯቸው የተወሰዱ ነጥቦች

ጠ/ር ዐብይ አህመድ በመደመር መጽሀፍ ምረቃ ላይ ከተናገሯቸው የተወሰዱ ነጥቦች
***
• ውስኪ ጠጪ ኢህአዴጎች እባካችሁ ውሃ መጠጣት የናፈቀው ህዝብ አለና አትርሱ ይላል መደመመር፤

• በድጋሜ ላረጋግጠላችሁ የምወደው ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች፤ ካለችበት ከፍት ትላለች፤ ኢትዮጵያ እንዳትበለጽግ የሚፈልጉ ይጠፋሉ እንጂ ኢትዮጵያ አትጠፋም፤

• የኢህአዴግ ውህደት መጨፍለቅ ነው የሚሉ አሉ፤ ይሄ ስህተት ነው፤ እውነት ነው ካልን በትግራይም በአማራም በደቡብም ያሉ ገዥ ፓርቲዎች ሌሎችን ብሄሮች ጨፍልቀው ነው የኖሩት ማለት ነው፤

• መደመር መባላትን ያመጣል የሚል አለ፤ ጎበዝ የሆነ ሰው ውስኪውን አስቀምጦ መባዛት የሚል መጽሀፍ ይዞ ይምጣ፤

• እኔ ያልኩት ካልሆነ አገር ይፈርሳል ማለት የ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያረጀ አስተሳሰብ ነው፤

 

• ከአመት እስከ አመት በ5 ሺህ ብር ደመወዝ ሆቴል እየተመገብክ ዳቦ የራበውን ህዝብ አስብልሃለሁ ማለት ቀልድ ነው፤

• ኢህአዴግ እንዴት እንደሚዋሀድ ምን ስም ይዞ እንደሚመጣ ሃሳብ አቀርባለሁ ዴሞክራት መሪ ስለሆንም እኔ አልወስንም የተወሰነውን በቅርቡ ለህዝቡ እንገልጻለን፤

• መደመር እያንዳንዱ ዜጋ አገሬን መምራት እችላለሁ የሚል እሳቤን የያዘ ነው፤
• የሚቀጥለው ምርጫ የምናላግጥበት ሳይሆን የተሻለ ሀሳብ ይዘን የምንወዳደርበት ይሆናል፤

• ኢትዮጵያዊያን መገዳደል የለብንም በሀሳብ ነው መታገል ያለብን፤

• ሰላም ሰላም የምንለው ጦርነትን ስለምንፈራ ሳይሆን ሰላምን አብዝተን ስለምንወድ ነው፤

• ከኤርትራ ወንድም ህዝብ ጋር የጀመርነው ጉዞ ወደ ብልጽግና እናደርሰዋለን እንጂ ወደኋላ አንልም፤

• 99 በመቶ አማኝ ህዝብ ያለበት አገር መሪ ሆኖ እምነትን ማራከስ አይቻልም፤ በማርክስና በሌኒን ፍልስፍ አይናችን አልታወረም፤ በፈጣሪ ልዕልና እናምናለን፤

• የኖቤል የሰላም ሽልማቱ የእናንተ የኢትዮጵያዊያን ነው፤ በቅርቡ ደግሞ ኢትዮጵያ በህዋ ውስጥ የራሷ ሳተላይት እንዲኖራት እየሰራን ነው፤(ምንጭ:- ኢኘድ)

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top