Connect with us

ከእንጂባራ በቅርብ ርቀት ዘንገና ሀይቅ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ 10 ሰዎች ህይዎት አለፈ

Amhara Mass Media Agency
ፎቶ፦ በሳሙኤል አማረ

ማህበራዊ

ከእንጂባራ በቅርብ ርቀት ዘንገና ሀይቅ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ 10 ሰዎች ህይዎት አለፈ

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ባንጃ ወረዳ ከእንጂባራ በቅርብ ርቀት የሚገኘው ዘንገና ሀይቅ አካባቢ በተከሰተ የተሽከርካሪ ግጭት አደጋ የሰዎች ህይዎት አልፏል።

አደጋው የተከሰተው ከባሕርዳር የተነሳ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስና ከቲሊሊ ወደ እንጂባራ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ የነበረ ሚኒባስ ዛሬ ከጠዋቱ 12:00 ላይ ፊት ለፊት በመጋጨታቸው መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል። የአደጋዉ ምክንያትም እየተጣራ መሆኑን የባንጃ ወረዳ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ዋና ሳጅን ዘመኑ ቅዱስ ለአብመድ ገልፀዋል።

በአደጋው የሚኒባሱን አሽከርካሪ ጨምሮ የ10 ሰዎች ህይዎት አልፏል፤ ከሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ አምስት መንገደኞች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ እንጂባራ ሆስፒታል ተወስደዋል ብለዋል ዋና ሳጅን ዘመኑ።

በአውቶብሱ ውስጥ የነበሩ ሁሉም መንገደኞች እና አሽከርካሪው ምንም አካላዊ ጉዳት እንዳልደረሰባቸውም የትራፊክ ተቆጣጣሪው ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ አስማማው በቀለ

Source: Amhara Mass Media Agency

  • Amhara Mass Media Agency
  • Amhara Mass Media Agency
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top