Connect with us

የማኅጸን በር ካንሰር ክትባት መድኃኒት ተሰራጨ

የማኅጸን በር ካንሰር ክትባት መድኃኒት ተሰራጨ
ALAMY

ነፃ ሃሳብ

የማኅጸን በር ካንሰር ክትባት መድኃኒት ተሰራጨ

የኢትዮጵያ መደሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲው ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ለሚካሄደው የማኅጸን በር ካንሰር ክትባት ዘመቻ የሚውል የማኅጸን በር ካንሰር ክትባት /Human Papilloma Virus Vaccine/ መድኃኒት አሠራጨ።

መድኃኒቶቹ ከ179 ሚሊየን 396 ሺ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሆኑን የክትባት ፕሮግራም መድኃኒት ክትትል ባለሞያ ወ/ት ናዲያ ሲራጅ ገለጹ፡፡

እንደ ባለሙያዋ ገለፃ የመድኃኒቶቹ ስርጭት በሁሉም የሀገሪቷ ክልሎች ለ1000 ወረዳዎች መካሄዱንና ከ1 ሚሊየን 350 ሺ በላይ ብዛት አላቸው፡፡

ወ/ት ናዲያ አክለውም የክትባት መድኃኒቶቹ ከ14 ዓመት በላይ ላሉ 1 ሚሊየን 286 ሺ 160 ሴቶች እንደሚሠጥ አብራርተዋል፡፡

የክትባት መድኃኒት ስርጭቱ በሚፈለገው የሙቀት መጠን ከ2 እስከ 8 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሆኖ ተሰራጭቷል ሲሉ
ወ/ት ናዲያ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top