Connect with us

ከንቲባ ታከለ ዑማ ከሥልጣናቸው እንደማይነሱ ተነገረ

ከንቲባ ታከለ ዑማ ከሥልጣናቸው እንደማይነሱ ተነገረ
የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት

ፓለቲካ

ከንቲባ ታከለ ዑማ ከሥልጣናቸው እንደማይነሱ ተነገረ

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ታከለ ዑማ ከሥልጣናቸው እንደማይነሱ አንድ ለኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ቅርበት ያላቸው ግለሰብ ተናገሩ።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማን በመምራት ላይ የሚገኙት አቶ ታከለ ከሥልጣናቸው ይነሳሉ የሚሉ ዘገባዎች ባለፉት ጥቂት ቀናት በሰፊው ተሰራጭተው ነበር።

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከትናንትናው በአዲስ አበባ ውይይት በማድረግ ላይ ነው።

ፓርቲው የአቶ ታከለ ዑማን ጨምሮ በተወያየባቸው ጉዳዮች ላይ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ፓርቲው በሚሰጠው መግለጫ ጠንከር ያሉ ጉዳዮችን እንደሚነሳ ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ ሰው ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

አቶ ታከለ ዑማ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር። ዋና ከተማዋን መምራት ከመጀመራቸው በፊት የኦሮሚያ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል። DW

 

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top