Connect with us

ታከለ ኡማ የአድዋ ጀግኖችን አመሰገኑ

Photo: EBC

ጥበብና ባህል

ታከለ ኡማ የአድዋ ጀግኖችን አመሰገኑ

★ ታከ ኡማ (ኢንጂነር) በዚሁ ፕሮግራም ላይ በተለይ አንዳንድ አክራሪ ብሔርተኞችን ጭራ ሊያስበቅል የሚችል ታሪካዊ ንግግር አድርገዋል

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ አዲስአበባ ከተማ አስተዳደርን እንዲመሩ ከተሾሙ አንድ ዓመት ተኩል ያስቆጠሩት ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከኃላፊነታቸው እንደሚነሱ ይፋዊ ያልሆኑ ምንጮቻንን አረጋግጠዋል፡፡ ምክትል ከንቲባው ለመነሳታቸው አንዱ ምክንያት አዴፓ( የቀድሞ ኦህዴድ) ከጀርባ ሆነው እንደሚያሸከርክሩ የሚገመቱ ግለሰቦች እንዳልተወደዱ ምንጮቻችን ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባው በትላንትናው ዕለት ከሚድሮክ ኢትዮጵያ በተመለሰው ቦታ ላይ (ፒያሳ አካባቢ) የአድዋ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

ታከ ኡማ (ኢንጂነር) በዚሁ ፕሮግራም ላይ በተለይ አንዳንድ አክራሪ ብሔርተኞችን ጭራ ሊያስበቅል የሚችል ታሪካዊ ንግግር አድርገዋል፡፡ ስም ሳይጠሩ የአጼ ሚኒሊክን ድንቅ ተግባር አክብረዋል፤ አወድሰዋል፡፡ በዚሁ ንግግራቸው ከ124 ዓመታት በፊት በአድዋ መሰዋዕትነት የከፈሉ አባቶችና እናቶች፣ አያቶቻችንንም አመሰግነዋል፡፡ አባቶችና እናቶቻችን አድዋ ድል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የአሸናፊነት ስሜትን ያወረሱበት ነው ብለዋል፡፡ የእኛ አባቶችና አያቶች በአድዋ በቀላኪዳን ተነስተው በደም በአጥንት ኢትዮጵያውያን እንዳንለያይ በትልቅ ሰንሰለት አስተሳሰረውናል፡፡ አባቶቻችንን፣ አያቶቻችን በዚያ ጊዜ ለናጻነታቸው መሰዋዕትነት ባይከፍሉ ኖሮ በአዲስአበባ ምድር በዚህ ደረጃ ቆመን ገድሉን ማውራት ባልቻልን ነበር ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ (ሙሉ ንግግራቸውን በቪዲዮው ላይ ማግኘት ይቻላል)

የዓድዋ ማዕከል በውስጡም ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በጥቂቱ ፦

• የአድዋ ሙዚየም

• ከ2 ሺህ ሰው በላይ የሚይዝ የዓድዋ አዳራሽ

• እያንዳንዳቸው 400 ሰው የመያዝ አቅም ያላቸው ሶስት(3) አዳራሾች

• የሲኒማ አዳራሽ

• ቤተ-መፅሐፍ

• የስፖርት ማዘውተርያዎች እና ጂሞች

• የህፃናት መጫወቻ እና የማቆያ ስፍራ

• የጌጣጌጥ መደብሮች

• የቤተ-ስዕል ማዕከላት

• ዘመናዊ የባስ እና የታክሲ ማቆሚያ

• ከ600 መቶ መኪና በላይ የመያዝ አቅም ያለው ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ

• ካፌዎች እና የምግብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት

• ለንባብ አገልግሎት የሚሆኑ የአረንጓዴ ስፍራ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

ማዕከሉ የውስጥም ሆነ የውጪ ይዞታው ለመዝናኛ የተመቸ ሲሆን፥ በውስጡም “ሁሉም ከዚህ ይጀምራል!” የሚል የአዲስ አበባ ከተማ ‘ዜሮ ኪሎ ሜትር’ በአንድ ኪ.ግ ወርቅ ምልክት እንደሚቀመጥበት የፋና ዘገባ ያስረዳል፡፡

Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top