Connect with us

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በህዳሴው ግድብ ላይ የሰጡትን አፍራሽ መልእክት ለመቃወም የበይነመረብ የፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በህዳሴው ግድብ ላይ የሰጡትን አፍራሽ መልእክት ለመቃወም የበይነመረብ የፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ
Photo: Social Media

ነፃ ሃሳብ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በህዳሴው ግድብ ላይ የሰጡትን አፍራሽ መልእክት ለመቃወም የበይነመረብ የፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በህዳሴው ግድብ ላይ የሰጡትን አፍራሽ መልእክት ለመቃወም የበይነመረብ የፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት በዛሬው እለት በየነ መረብን (online petition) በመጠቀም የተቃወሞ ፊርማን መሰብሰብ የሚያስችል አዲስ አሰራር ይዞ ቀርቧል።

ጽህፈት ቤቱ ባለፈው ሳምንት ”ግብፆች ግድቡን ያፈነዱታል” በማለት ዶናልድ ትራምፕ የተናገሩትን ግዴለሽ ንግግር ተከትሎ፣ ሁለት አይነት የበየነ መረብ ፊርማ ማሰባሰቢያ ድረገፆችን አዘጋጅቶ የፊርማ ማሰባሰብ ስነስርአተን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።

የመጀመሪያው ”we the people” የሚል ድረ ገጽ ሲሆን፣ አቤቱታን ማሰሚያ መድረክ አማካኝነት የአሜሪካው ዋይት ሀውስ ላይ የተኮረ ነው ተብሏል።

ሁለተኛው ደግሞ ”change.org” የሚል ድረ ገጽ ሆኖ፣ አለም አቀፋዊ ማህበረሰቡን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

የፊርማ ማሰባሰቢያ ስነ ስርዓቱን ያሰጀመሩትና የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አረጋዊ በርሄ እንዳሉት፣ ፅህፈት ቤታቸው ላለፉት አመታት በተቀናጀ መልኩ ለግድባችን ግንባታ የሚያስፈልገውን ገንዘብ በማሰባሰብ በቁርጠኝነት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው፣

በመሆኑም ”ሁሉም ኢትዮጵያን፣ ትውለደ ኢትዮጵያዊንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ ይህንን የበየነ መረብ የፊርማ ማሳሰብያዎች በመጠቀም፣ ፊርማቸውን እንዲኖሩና በፕሬዝዳንት ትራምፕ ንግግር ሳቢያ የተሰማቸውን ንዴትና ተቃውሞ እንዲገልጹም” ጠይቀዋል።

በተለይ ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን እነዚህን ድረገፆች ለሁሉም ሰዎች በሙሉ ተደራሽ እንዲያደርጉ ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ ከ150 የሚበልጡ ሰዎች ፊርማቸውን በመፈረም የትራምፕን አስተያየት መቃወማቸውን የገለፁ ሲሆን በ 1 ሳምንት ውስጥ ብቻ መቶ ሺህ ሰዎች ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top