Connect with us

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ የከንቲባዎች ፎረም የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተመረጡ

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ የከንቲባዎች ፎረም የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተመረጡ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ የከንቲባዎች ፎረም የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተመረጡ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ምክትል ከንቲባ  ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ የከንቲባዎች ፎረም የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተመረጡ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር “የተሻለ ከተማ ለተሻለ ሕይወት” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ ከንቲባዎች በቋሚነት ተገናኝተው ስለከተሞች ጉዳይ የሚመካከሩበት፣ የእርስ በርስ ትስስር የሚፈጥሩበት፣ በችግሮች ዙሪያ በጋራ መፍትሔ የሚፈልጉበት መድረክ ለማመቻቸት በአዲስ አበባ ከተማ የኢትዮጵያ ከንቲባዎች ፎረም ተመስርቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ምክትል ከንቲባ  ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢትዮጵያ የከንቲባዎች ፎረም ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡ ሲሆን የቦርዱ ሥራ አስፈጻሚዎች 7 አባላት አሉት።

በዚሁ መሠረት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ም/ከንቲባ (የቦርዱ ሰብሳቢ)፣ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን የሐዋሳ ከተማ አስተዳዳር ም/ከንቲባ (ምክትል ሰብሳቢ) እንዲሁም ዶ/ር ድረስ ሣህሉ የባህዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ (ጸሐፊ) ሆነው ተመርጠዋል።

የአዳማ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ፣ የአሶሳ፣ የድሬደዋ እና ደገሀቡር ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች የቦርዱ አባላት ሆነዋል።

የቦርዱ የሥራ ዘመን ሁለት ዓመት መሆኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሰክሬታሪያት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል። (EBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top