Connect with us

ክቡር ዶክተር ለማ ጉያ፤ ሀገረሰባዊው ዕንቁ፡፡

ክቡር ዶክተር ለማ ጉያ፤ ሀገረሰባዊው ዕንቁ፡፡
Photo: Social Media

ጥበብና ባህል

ክቡር ዶክተር ለማ ጉያ፤ ሀገረሰባዊው ዕንቁ፡፡

ክቡር ዶክተር ለማ ጉያ፤
ሀገረሰባዊው ዕንቁ፡፡
(ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ)

ሰውዬው ሀገር ምናባቸው ላይ ያተሙ ጥበበኛ ናቸው፡፡ ቀለም ካነሱ ምድሯን ይፈጥሩታል፡፡ ሀገርኛ ሰው ይወዳሉ፡፡ ሀገር በጥበብ አኑረዋል፡፡ የአቶ ጉያ ልጆች ሀገር ወዳድ ዜጎች ናቸው፡፡ አንዱ ደግሞ የክቡር ዶክተሩ ለማ ጉያ፡፡

መጀመሪያ ያየሁት የሰዓሊ ለማ ጉያ የዐጼ ምኒልክ ሥራ ዛሬም የማይረሳኝ ምስል ነው፡፡ የሰዓሊ ለማ ጉያን ሥራዎች ያየ ወደ ሀገሩ መስኮች ይቀርባል፡፡ የተሰቀለ ቆዳ ስር ቆሞ በምናብ ወደ ውብ መስኮች ይሄዳል፡፡

ሰውዬው ቡርሽ ሲያነሱ ሀገር አይጠባቸውም፡፡ ከስሜን ተከዜ ጫፍ እስከ ባሮ ኦፔኖ የሚጓዙ የሀሳብ ሰው ናቸው፡፡
ከመቅደላ አምባ ቆመው ለሀገር ክብር የተከፈለን መሥዋዕትነት በውብ ቡርሽ አኑረውልናል፡፡ ጀግኖቻቸውን አይደለም በሰፈር በኢትዮጵያ አይገድቡም፤ እንቁ የአህጉሪቷ ጥቁሮች በስራቸው ነፍስ ዘርተዋል፡፡

የእርሻ ውሎ፣ የእሬቻ ክብረ በዓል፣ ጥምቀትና ማህበራዊ መስተጋብሮቻችን ከቡርሽ ስራዎቻቸው ከቆዳ ላይ ጥበባቸው አላመለጡም፡፡ ያልገለጹት እኛነት የለም፡፡ ታሪክን በሥዕል እንደሰነዱልን ከማምንባቸው ሰዎች አንዱ ናቸው፡፡

በህይወት ዘመናቸው በአስር ሺህ የሚቆጠር የሥዕል ሥራዎችን ለኢትዮጵያ አበርክተዋል፡፡ በሥዕል ሀገርን በማስተዋወቅ በኩል አያሌ የውጪ ጎብኚዎችንና ዲፕሎማቶችን ደርሰዋል፡፡ ኢትዮጵያን ሸራ ላይ ለትውልድ አስቀርተው በጥበብ አስጊጠዋል፡፡ ሰውዬው የሀገር ሰው ነበሩ፤

ለማ ጉያ ክቡር ዶክተር ብቻ አይደሉም፤ ሰዓሊም ብቻ አይደሉም፡፡ ወታደርም ናቸው፡፡
ሻምበል፤ የአየር ኃይል አባል፡፡ ለሀገር ዋጋ መክፈል ምን እንደሆነ የሚያውቁ፤ ከሙያቸው ባለፈ ህይወትን ለእናት ሀገር በመስጠት ሥርዓት የተሰሩ፤


ሰዓሊውና የሰዓሊያኑ አባት ለማ ጉያ 92 ዓመታትን ከኖሩባት ምድር እንደተከበሩ ተሸኝተዋል፡፡ የደብረ ታቦር ዋዜማ ነሐሴ 12 ቀን 1921 ዓ.ም. የተወለዱት ኢትዮጵያዊ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡


ለማ ሀገር የመሳል ብቻ ሳይሆን ሀገር የመውደድ ምልክት የሀገረሰባዊው እሴት መገለጫ ቅርስና መስህብ የሆኑ ሥራዎች ፈጣሪ ነበሩ፡፡ ዘለዓለማዊ የሰላም እረፍት ለክቡር ዶክተር ሰዓሊ ለማ ጉያ፤ መጽናናትን ለመላው ቤተሰባቸው እመኛለሁ፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top